“እኩል ምላሽ አትስጪኝ/ጠኝ! ፣ ታደገልኝ!

- Advertisement -
Sidebar AD

፣ አሁንማ ተደረሰ! ኡፍ….ኡፍ.. ”

ታዳጊ ልጆች ያላቸው ወላጆች ከልጆቻቸው ጋር ያለውን አለመግባባት ከሚገልጹበት ንግግር መካከል ይገኝበታል፡፡

እድገትን መገንዘብ

የልጆች አእምሮ እንደ ደህንነት ካሜራ
( Surveillance Camera ) የተሰጠውን መረጃ ይመዘግባል፤ ይሰበስባል፡፡ የተመዘገበው መረጃ በሚፈለገው ጊዜ ጥቅም ላይ እንደሚውል ሁሉ እድሜያቸው 13 ሲሆን በውስጠኛው የአእምሮ ክፍል ( Subconscious mind) የነበረውን መረጃ በመገጣጠም
የራሳቸውን ትንታኔ መስጠት ይጀምራሉ፡፡

በዚህ ወቅት ታዳጊዎች መወያየት፣ መከራከርና ሃሳባቸውን መሰንዘርና ማሰላሰል ይጀምራሉ፡፡ለወላጅ ደግሞ ይህ የታዳጊዎች ባህሪ የወላጅነት ክብርን የሚፈታተን ተደርጎ ይወሰዳል፡፡

የተቃርኖ ህይወት

አብዛኛውን ጊዜ ታዳጊዎች የቅርብ ሰዎቻቸውንና
የሚወዷቸውን ሲያበሳጩ ይስተዋላል፡፡ ታዳጊዎቹ ይህንን የሚያደርጉት ከጥላቻ የመነጨ ሳይሆን ከእድሜ እድገታቸው ተከትሎ በሚከሰትየስሜት መዋዠቅ (Mood swings) ነው፡፡ በዚህ ወቅት ታዳጊዎች የተዘበራረቀና ግራ የሚያጋባ ስሜት ያስተናግዳሉ፡፡ ለምሳሌ ቁጣ፣ ብስጭት፣
መናደድ…ይህንን ስሜት እንዴት መግለፅ እንዳለባቸው አለማወቃቸው ከቤተሰብ ጋር የአለመግባባት ምክንያት ይሆናል፡፡

የአፍላ እድሜ ተግዳሮቶች

ታዳጊዎች ካሉባቸው ተግዳሮቶች መካከል አቻ ግፊትናስሜታዊነት በዋናነት ይጠቀሳሉ፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ታዳጊዎች ከአዋቂዎች በተለየ መልኩ ያስባሉ፡፡ አዋቂዎች አመክንዩን
( Reasoning) ሲጠቀሙ ታዳጊዎች ደግሞ ስሜታዊነት የነገሰበት ይሆናል፡፡

ታዳጊዎችን መረዳት (Understanding Teens)

ታዳጊነት የሽግግር የህይወት ምዕራፍ ሲሆን ህጻንምአይደሉም አዋቂም አይደሉም፡፡ ማንነታቸውን ፍለጋ ላይ የተጠመዱ በመሆናቸው በርህራሄና በፍቅር ልንረዳቸው ይጠበቅብናል፡፡

መውጫ ፦ ታዳጊዎችን የምናይበት አመለካከት (Attitude) ከእነርሱ ጋር ያለንን ግንኙነት ይወስናል።

✍️ ብርሃኑ በላቸው አሰፋ
[https://t.me/childdevtnetwork]
Admin



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1