የውጭ ምንዛሬ መጨመሩ የኩላሊት እጥበት ህክምናና የመድኃኒት ዋጋ ጭማሪ ማስከተሉ ተነገረ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የውጭ ምንዛሬ በመጨመሩ ምክንያት የዴያሌሲስ ዋጋን በየቦታው ጭማሪ ማሳየቱ ተጠቁሟል።

በተጨማሪም የኩላሊት ታማሚዎች የሚጠቀሟቸው መድኃኒቶች ዋጋ መጨመሩ እንዲሁም ድጋፍ ሰጪ አካላት መቀነስ እና ህብረሰቡ ድጋፉን አጠናክሮ መቀጠል ላይ መዘናጋት መኖሩ ህመምተኞች እየተቸገሩ መሆኑን የኩላሊት ህመምተኞች እጥበት በጎ አድራጎት ድርጅት ስራ አስኪያጅ ዶክተር ሰለሞን አሰፋ ለብስራት ሬዲዮ እና ቴሌቭዥን ተናግረዋክ።

ዶክተር ሰለሞን አክለው እድሜያቸው ከ40 ዓመት በላይ የሆኑ ማንኛውም ግለሰብ በየአመቱ አንድ ጊዜ ምርመራ በማድረግ የኩላሊት ደረጃቸውን እንዲያውቁ ጥሪ አቅርበዋክ።

10 ከመቶ እስከሚደርስ ድረስ የኩላሊት መድከም ስለማይታወቅ በቅርብ ባለ ጤና ተቋም በመሄድ ምርመራ እንዲያደርጉ እንዲሁም እድሜያቸው ከ40 አመት በታች የሆኑ ሰዎች ደግሞ በሁለት አመት አንዴ ምርመራ እንዲያደርጉ በማንሳት ስኳር እና ደምግፊት ያለባቸው ሰዎች ደግሞ በየስድስት ወሩ ምርመራ ማድረግ እንዳለባቸው አሳስበዋል።

አያይዘውም በሚኒባስ ላይ በመሆን ድጋፍ በመጠየቅ የሚያጭበረብሩ አንዳንድ አካላት በመኖራቸው ሌሎች ድጋፍን የሚፈልጉ ህመምተኞች ድጋፍ እንዳያገኙ እንቅፋት እየሆኑ ይገኛል ብለዋል።

ህብረተሰቡ በሚፈጠርበት ጥርጣሬ ትክክለኛ ድጋፍ ለሚያሻቸው ሰዌች እንቅፋት እንደሆኑ ገልፀዋል። በመሆኑ ድጋፉን ተቋማዊ አድርገው ለህሙማኑ በመድረስ በቋሚነት ድጋፍ ማድረግ እንዲቻል ዶክተር ሰለሞን አሰፋ ጥሪ አቅርበዋል።
#ዳጉ_ጆርናል
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2