#FastMereja I በቲክቶክ ማህበራዊ ሚዲያ የሚታወቀው ባርኮት (በመታወቂያ ስሙ ክሊንተን) የወርሃ ግንቦት የ“ቅን ልቦች” ተሸላሚ ሆኗል።
ይህ የወርሃዊ ሽልማት መርሃ-ግብር በማህበረሰቡ ውስጥ አዎንታዊ ተፅዕኖ ለሚያሳድሩ ግለሰቦች እውቅና ለመስጠት የሚዘጋጅ ሲሆን፣ ወጣቱ የቲክቶክ ተፅዕኖ ፈጣሪ ባርኮት በግንቦት ወር ባከናወናቸው ተግባራት አሸናፊ መሆን ችሏል። ሽልማቱን ከተቀበለ በኋላ ባደረገው ንግግር፣ የማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ለበጎ ተግባር መዋል እንዳለባቸው አጽንኦት ሰጥቷል። በተለይም በዲጂታሉ ዓለም ውስጥ ያሉ ወጣቶች የሀገር ባለውለታዎችንና ታላላቆችን በማክበር ረገድ ግንባር ቀደም መሆን እንደሚገባቸው አሳስቧል።
Source: FastMereja








No comments yet.