“ ጦቢያ “ በመላዉ አዉሮፓና ዮናይትድ ኪንግደም የጥበብ መድረክ ለማዘጋጀት ከሆፕ ፎር ፒፕል “ ከተባለ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር ተፈራረመ
#Ethiopia | ላለፉት 13 ዓመታት በኪነ – ጥበብ መድረክ ከፍተኛው ዕውቅናን ያተረፈው ጦቢያ ግጥም በጃዝ የተሰኘው መድረክ በቅርቡ ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በመላው አውሮፓ ከተሞች ልዩ ልዩ የኪነ ጥበብ ትዕይንቶችን “ኢትዮ-አውሮፓ የባህል፣ የኪነ-ጥበብ እና የህዝብ ግንኙነት” በሚል መጠሪያ ልዩ የጥበብ ዝግጅቱን መሠረቱን በጀርመን ሀገር ካደረገውና ራዕዮን ችግረኛ ልጆች እና ወጣቶች በራሳቸው የሚተማመኑ ዜጋ እንዲሆኑ ማስቻል ነው በማለት ከሚንቀሳቀሰው ሆፕ ፎር ኢትዮጵያ ፑፒልስ መንግስታዊ ያልሆነ ግብረሰናይ ድርጅት ጋር የመግባቢያ ሰነዱን ተፈራርመዋል፡፡
በስምምነቱ ሁለቱም ወገኖች የኢትዮጵያን እና የአውሮፓ የባህል እንዲሁም የስነ ጥበብ ግንኙነት ለማሳደግ የፈለጉ ሲሆን፣ ዓላማቸውም የኢትዮጵያውያንን እና የአውሮፓውያንን አንድነትን፣ ወንድማማችነትን እና የገጽታ ግንባታን የሚገልጹ የቀጥታ መድረክ ኪነ ጥበባዊ ትዕይንቶችን በተለያዩ የአውሮፓ ከተሞች በማዘጋጀትና በማቅረብ እንዲሁም ማህበራዊ ሚዲያ በመጠቀም የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ማጠናከር እንደሆነ የድርጅቶቹ ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች ገልፀዋል፡፡
የላይዳ መንሽ መልቲሚዲያ / ጦቢያ ዋና ስራ አስኪያጅ ገጣሚ ምሥራቅ ተረፈ እንደገለፁት ይህ የጥበብ ቡድን ከጥበባዊ ስራዎቹ በተጨማሪ በእንደዚሀ ዓይነት የእርዳተ ስራዎች ላይ አስተዋፅኦን ማበርከት የጦቢያ የኪነ ጥበብ ቡድን አንዱ ዋነኛ ዓላማ እንደሆነና ዩናይትድ ኪንግደምን ጨምሮ በመላው አውሮፓ ከተሞች የሚገኙ ዝግጅቱን የሚታደሙ ኢጥዮጲያውያንና ትውልደ ኢትዮጲያውያን በመድረክ ዝግጅቱ ሲገኙ ከመዝናናት ባለፈ እያንዳንዱ ታዳሚ የትምህርት ዕድልን ላላገኙና ለሌሎቸም ለተጨገሩ ከፍተኛ አስተዋፅኦም እያደረጉ እንደሆን እያሰቡ ዝግጅቱን እንዲታደሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ትምህርት ቤት ለመማር አቅም የሌላቸውን ለትምህርት ቤት ልጆች እና ለቤተሰቦቻቸው አስፈላጊ ቁሳቁሶችን ማቅረብ በተጨማሪነትም ለጎበዝ ተማሪዎች የከፍተኛ ትምህርት እና የስኮላርሺፕ እድሎችን እየሠጠ የሚገኘው ሆፕ ፎር ኢትዮጵያ ፑፒልስ በኢትዮጲያ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሆኑት አቶ ዘውዱ ገዛኸኝ በበኩላቸው ከዚህ ቀደም ሲሰራባቸው ከነበሩ የገንዘብ ማሰባበሲየ መንገዶች በተለየ በዚህ ስምምነት ዜጎች በእንደዚህ ያሉ የመዝናኛ ሁነቶች ሀራቸውንና ህዝባቸውን ድጋፍ እንዲያደርጉ ማስቸል ለድርጅቱ ዓላማ መሳካት ከፍተኛ ሚናን ይጫወታል ብለዋል፡፡
ይህን የመግባቢያ ስምመነት ሰነድ በሚዲያ አጋርነት አርትስ ቴሌቪዥን የሚሰራ ሲሆን ስምምነቱም በሚዲያው ቅጥር ተፈጽሟል፡፡



Source: GetuTemesgen









No comments yet.