#Ethiopia | ሁለት ወጣት ጥንዶች ፍቅር ከጀመሩ ወዲህ የመጀመርያ አደጋ እንደገጠማቸው ለመግለፅ በፊታቸውና ጭንቅላታቸው ላይ የደረሰባቸውን አደጋ የሚያሳይ ምስል ከፍቅሬ ጋር የመጀመርያ አደጋችን የሚል ፅሑፍ አክለው በፌስቡክ ላይ ማጋራታቸውን ተከትሎ መነጋገርያ ሆነዋል።
አነጋጋሪው የፌስቡክ ልጥፍ ጥንዶች በምን ያህል ደረጃ በእለት ተእለት ህይወታቸው ላይ የሚገጥሟቸውን ነገሮች በማህበራዊ ትስስር ገፆቻቸው ላይ ማጋራት አለባቸው በሚል ክርክር አስነስቷል።
በተለይ ደግሞ የልጥፉ ባለቤት የሆነቺው እንስት ስለ አደጋው አስከፊነት ሳይሆን ከፍቅር አጋሯ ጋር በመሆን ያሳኩት ነገር አስመስላ ልጥፉን ማጋራቷ በርካቶችን አስከፍቷል።
የሚታዩ የአደጋ ጉዳቶች የያዘው የፌስቡክ ልጥፍ ቫይራል ለመሆን ጊዜ አልፈጀበትም። ነገር ግን ልጥፉ ጥንዶቹ በጠበቁት መንገድ አልነበረም ቫይራል የሆነው። በተጋራው ምስል አንድ ጭንቅላቱን በቫንዴች የተጠቀለለ ወጣትና አንዲት ግንባራ፣ አፍንጫዋና እጇ በፕላስተር የተለጣጠፈች ወጣት የሚያሳይ ሲሆን ከስሩ የተፃፈው ነገር ግን ስለአደጋው አስከፊነት ሳይሆን ጥንዶች አብዛኛውን ጊዜ ለመጀመርያ ጊዜ ከፍቅረኛዬ ጋር እንዲህ አደረግን እንደሚሉት ሁሉ ለመጀመርያ ጊዜ ከፍቅረኛየ ጋር አደጋ አጋጠመን የሚል ፅሑፍ ነበር የነበረው። ታዲያ ለስላቅ ወደኃላ የማይለው የማህበራዊ ትስስር ገፆች አስተያየት ሰጪም በአደጋው ጥንዶቹ አንድን የህይወት እቅድ ያሳኩ እስኪመስል ድረስ የእንኳን ደስ አላቹ መልእክት ለማስተላለፍ ጊዜ አልፈጀበትም።
ነገር ግን ይህ ያልተለመደ ክስተት የማህበራዊ ትስስር ገፅ ተጠቃሚዎችን በሁለት ጎራ ከፍሏል።አንዳንዶች የጥንዶቹን ችግርን ቀለል አድርጎ የማለፍ ጥበብ ሲያደንቁ የተስተዋሉ ሲሆን ሌሎች ደግሞ ለአሁን ጊዜ ወጣቶች ሁሉም ነገር ቀልድና ላይክ መሰብሰብያ መንገድ ነው ሲሉ አስተያየት ሲሰጡ ተስተውለዋል።
ሌሎች ደግሞ የአሁን ግዜ ፍቅር ከሌሎች ነገር በላይ በማህበራዊ ትስስር ገፆች ላይ ተወዳጅና ትኩረት የሚስቡ ጥንዶች መሆንን ይመርጣሉ ያሉ ሲሆን ገሚሶቹ ደግሞ ፍቅር ማለት ሀዘንና ደስታ መጋራት ነው ደግ አደረጉ ሲሉ ተደምጠዋል።
በጥንዶቹ የፌስቡክ ልጥፍ ከተቀመጡ አስገራሚ አስተያየቶች ደግሞ “ፍቅር ከጀመራቹ ወዲህ የመጀመርያ አደጋ ስለገጠማቹ ደስ ብሎኛል፤ ሁለተኛውን በጉጉት እጠብቃለው” የሚለውን የበርካቶችን ቀልብ ስቧል።
#ዳጉ_ጆርናል
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።
“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet
ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26
ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet
ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet
ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet
ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet
አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et
ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et
Source: GetuTemesgen









No comments yet.