ሀዋሳ ቅዱስ ገብርኤል
በሀዋሳ ደብረ ምህረት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም ሐምሌ 19 በደማቅ ሁኔታ የሚከበረውን የቅዱስ ገብርኤል ንግስ በዓልን ተከትሎ፣ ወደ ቅዱስ ገብርኤል (ሱሙዳ አደባባይ) የሚወስዱ ዋና ዋና መንገዶች እንደሚዘጉ የሀዋሳ ከተማ ፖሊስ መምሪያ አስታውቋል።
እንደ ፖሊስ መረጃ፣ ከዛሬ ሐምሌ 18 ቀን 2018 ዓ.ም ከአሁን 9:00 ጀምሮ በዓሉ ተጠናቆ እስኪያበቃ ድረስ ወደ ቅዱስ ገብርኤል (ሱሙዳ አደባባይ) ከሁሉም አቅጣጫ የሚያስገቡ መንገዶች ለሁሉም የትራፊክ እንቅስቃሴ ሙሉ በሙሉ ዝግ ይሆናሉ።
– ከሳውዝ ስታር (መስቀል አደባባይ)፣
– ከሰሜናዊ ሲዳማ ዞን አስተዳደር፣
– ከትሩፋ በሎጊታ፣
– ከጤና ቢሮ (ማር ሲል)፣
– ከክብሩ ሆስፒታል፣
– ከፒያሳ ዳሽን ባንክ፣
– ከታቦር 1ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ወደ ገብርኤል (ሱሙዳ አደባባይ) የሚያቀኑ መስመሮች በሙሉ ይዘጋሉ።
ፖሊስ አሽከርካሪዎች የመንገድ መዘጋቱን አስቀድመው በመገንዘብ አማራጭ መስመሮችን እንዲጠቀሙ፣ ከፀጥታ አካላት ጋርም በመተባበር የትራፊክ መጨናነቅና አደጋ እንዳይከሰት አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርቧል።
@Seledadotio

No comments yet.