“ፋዘር አብድ ኤል መሲሕ” ይሏቸዋል ግብጻውያኑ፡፡

- Advertisement -
Sidebar AD

ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም ካላቸው ፍቅር የተነሳ እጅግ አደገኛ በረሀዎችን አቋርጠው ወደ በራሙስ ገዳም አቀኑ፡፡

ይህ በሰሜናዊ ግብጽ የሚገኝ ገዳም የቅድስት ድንግል ማርያም ገዳም ሲሆን የመጀመሪያ ስማቸው አባ ገብረ ጻድቅ የነበሩት በኋላም በገዳሙ አበ አባምኔት አባ ገብረ ክርስቶስ የተባሉት ኢትዮጵያዊ አባት ሀገራት አቋርጠው ነው ለመመንኮስ ወደዛ የተጓዙት፡፡ የቀደሙት ቅዱሳን አባቶቻችን በዚህ መልክ ለበርካታ ወራት በእግራቸው ተጉዘው በረከትን ይፈልጋሉ፡፡

እነሆ በዘመናችን ደግሞ ሁሉም ነገር በተመቻቸበት ቅዱሳን መካናትን መጎብኘት፣ ገዳማትን መሳለም ትልቅ በረከት የሚገኝበት ሆኖ በርካቶች ይህን ተግባር በፍቅር ይፈጽሙታል፡፡

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን ምስራቅ በለሳ ወረዳ የሚገኘውን ታላቅ የበረከት ስፍራ ሙት አንሳ ማር ቅዱስ ሚካኤል አንድነት ገዳም እነሆ እድል ተብለናል፡፡

በተለይ በዚህ የቅድስናና የጾም ወቅት ይህን መሰል መንፈሳዊ መካናትን መጎብኘት በጸጋ ላይ ጸጋን ይጨምራል፡፡ እስካሁን የስፍራውን ቅድስና ስንሰማ ቆይተናል፣ በሊቀ መልአኩ ፈቃድ የማይታለፍ ስፍራውን የመሳለምና ገዳማውያኑን የመጎብኘት ጊዜው አሁን ነው፡፡

ነፍሳችን የስጋችን ሩጫ እንዳይውጣት ስጋችንም መረጋጋትና ሰላም እንዲያገኝ ለጥቂት ቀናት ከዓለም ጫጫታ ፋታ እንውሰድ፡፡

የጉዞ መነሻ ቀን፡- መጋቢት 25 2017 ዓ.ም

የመመለሻ ቀን፡- ሚያዝያ 02 2017 ዓ.ም

የደርሶ መልስ ዋጋ፡- ምግብ፣ ትራንስፖርትና ማረፊያን ጨምሮ – 3500 ብር

ለበለጠ መረጃ፡- 0938 84 44 44


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: