በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የመድኃኒቶች ጥራትና ደህንነትን ለማረጋገጥ ያግዛል የተባለዉ አዲስ መመሪያ ወጣየኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒ…

- Advertisement -
Sidebar AD
☄️በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የመድኃኒቶች ጥራትና ደህንነትን ለማረጋገጥ ያግዛል የተባለዉ አዲስ መመሪያ ወጣ
የኢትዮጵያ ምግብና መድኃኒት ባለሥልጣን በሀገር ውስጥ የሚመረቱ የመድኃኒቶች ጥራትና ደህንነትን ለማረጋገጥ የሚያግዝ አዲስ መመሪያ አውጥቷል።
“የባዮኤክቫለንስ ጥናት ማዕከል እና የባዮአናሊቲካል ላብራቶሪ ቁጥጥር መመሪያ ቁጥር 1043/2017” ተብሎ የሚጠራው ይህ መመሪያ፣ በገበያ ላይ የሚውሉ የመድኃኒት ምርቶች ተመሳሳይ የፈዋሽነት እና የደህንነት ደረጃዎችን ማሟላታቸውን ለማረጋገጥ ያለመ መሆኑ ተጠቁሟል።
በተለይም በጽንስ ስም የሚመረቱ መድኃኒቶች ከታወቁ የመድኃኒት ምርቶች ጋር ተመሳሳይ የሆነ የፈዋሽነት እና የደህንነት ደረጃ እንዲኖራቸው ለማድረግ ያለመ ነው።
ይህ መመሪያ “ባዮኢኩዊቫለንስ” የተሰኘ ልዩ ጥናት በማድረግ በጽንስ ስም የሚመረቱ መድኃኒቶች ከታወቁ የመድኃኒት ምርቶች ጋር ያላቸውን ተመሳሳይነት ማረጋገጥ እንደሚጠበቅባቸው ይደነግጋል።
በተጨማሪም፣ መመሪያው የመድኃኒት
ማምረቻ ተቋማትና ላቦራቶሪዎች ፈቃድና ቁጥጥር ላይ እንደሚያተኩር ካፒታል ለመረዳት ችሏል።
መመሪያው በኢትዮጵያ የመድኃኒት ቁጥጥር ላይ ትልቅ ምዕራፍ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን፣ ለመድኃኒት ኢንዱስትሪው ዕድገት አስተዋጽኦ እንደሚያደርግ ይጠበቃል። በተጨማሪም፣ ለሕዝብ ተደራሽና ጥራት ያላቸውን መድኃኒቶች ለማቅረብ ያለመ ነው ተብሏል።
@seledadotio
@seledadptio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2