በቢሾፍቱ የኢትዮ ቴሌኮም የመሰረተ ልማት አውታር ላይ ዘረፋ የፈጸሙ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ጨለለቃ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በቢሾፍቱ የኢትዮ ቴሌኮም የመሰረተ ልማት አውታር ላይ ዘረፋ የፈጸሙ ግለሰቦች በእስራት ተቀጡ‼️
 
በቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ጨለለቃ ክፍለ ከተማ ውስጥ በኢትዮ ቴሌኮም የመሰረተ ልማት አውታር ላይ ዘረፋ የፈጸሙ ሁለት ግለሰቦች በእስራት እንዲቀጡ ተወስኗል።የከተማው አቃቤ ሕግ ጽሕፈት ቤት የኢኮኖሚ ነክ ወንጀሎች ምርመራ ሂደት እንዳስታወቀው፣ ተከሳሾች ሃሮን ዮሴፍ እና ተገኔ ተሾመ የኢትዮ ቴሌኮም ንብረት የሆኑ የሲሲቲቪ ኬብል ሽቦዎችን ዘርፈው ሊሰወሩ ሲሉ በቁጥጥር ስር ውለዋል።
 
ወንጀሉ የተፈጸመው በቢሾፍቱ ከተማ ጨለለቃ ክፍለ ከተማ ኤረር ወረዳ «ጎልደን ሆቴል» ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ከምሽቱ ሰባት ሰዓት ላይ መሆኑ ተገልጿል።ፖሊስ የምርመራ መዝገቡን አጠናቆ ለአቃቤ ሕግ የላከ ሲሆን፣ አቃቤ ሕግም የኢትዮ ቴሌኮም እና የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት መሰረተ ልማቶችን ለመጠበቅ የወጣውን አዋጅ ቁጥር 464/2005 አንቀጽ 4 ንኡስ አንቀጽ 4ን በመጥቀስ በቁጥጥር ስር በዋሉት ግለሰቦች ላይ ክስ መስርቶባቸዋል።
 
ጉዳዩን የተመለከተው የቢሾፍቱ ከተማ አስተዳደር ከፍተኛ ፍርድ ቤት፣ ተከሳሾቹ በሕዝብ መሰረተ ልማት ላይ የፈጸሙት የዘረፋ ወንጀል በአቃቤ ሕግ ማስረጃ በበቂ ሁኔታ በመረጋገጡ እያንዳንዳቸው በ4 ዓመት ጽኑ እስራት እንዲቀጡ ውሳኔ አስተላልፋል።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: