በክልሎች ለሚገኙ መስማት የተሳናቸው ዜጎች የተሟላ የሕክምና አገልግሎት አለመኖሩ ተገለጸ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በኢትዮጵያ በተለያዩ የክልል ከተሞች የሚገኙ መስማት የተሳናቸው ዜጎች በተሟላ ሁኔታ የሕክምና አገልግሎት እያገኙ አለመሆኑን የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች ኮሚሽን (ኢሰመኮ) አስታውቋል።

የኮሚሽኑ የሴቶች፣ ሕጻናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሃዋሪያ፤ ከተሟላ የጤና አገልግሎት እጥረት በተጨማሪ የሚሰጡ የሕክምና አገልግሎቶች ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቁ በመሆናቸው ምክንያት የሚያስፈልጋቸውን የሕክምና አገልግሎት ለማግኘት በገንዘብ እጥረት እየተፈተኑ እንደሚገኙ ተናግረዋል።

ኮሚሽነር ርግበ አክለውም፤ በሀገሪቱ ክልሎች ላይ ከሚገኙ መስማት የተሳናቸው ዜጎች ባሻገር፤ በአዲስ አበባ ከተማም ጭምር ማግኘት ያለባቸውን አገልግሎትን በበቂ ሁኔታ ለማግኘት የሚቸገሩበት ሁኔታ ስለመኖሩ ገልጸዋል፡፡

ለመስማት የተሳናቸው ዜጎች የጤና አገልግሎትን በተሟላ ሁኔታ በማግኘት ረገድ እንደ ክፍተት ከሚነሱ ጉዳዮች በተጨማሪ፤ መስማት የተሳናቸው ዜጎች የተለያያ መሰረታዊ አገልግሎቶችን ለማግኘት ሲቸገሩ ይስተዋላል ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

አክለውም በአገልግሎት ሰጪ ተቋማት ላይ ለመስማት የተሳናቸው ዜጎች ምቹ የሆነ የሥራ ሂደት እንዲኖር እና ተግባቦትን ለማሳደግ የምልክት ቋንቋ ተናጋሪ ግለሰቦች በተቋማት ላይ አገልግሎት እንዲሰጡ ከማድረግ አኳያ ክፍተቶች ስመኖራቸው ገልጸዋል፡፡

መስማት የተሳናቸው ዜጎች ከትምህርት፣ ከሥራ እና በጤና አገልግሎት ላይ ሲገለሉ የሚስተዋልበት አጋጣሚ መኖሩን የሚያነሱት ኮሚሽነር ርግብ፤ የመስማት ችግርን በተመለከተ ለሚነሱ ችግሮች የበጀት እጥረት እንደ ምክንያት የሚነሳ መሆኑን ጠቁመው የበጀት እጥረት ችግሩን በዘላቂነት መፍታት እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ የሚገኙ እና ለመስማት የተሳናቸው ዜጎች መስማትን እንዲሁም ለመናገር የሚያስችሉ የቴክኖሎጂ ውጤቶች ለዜጎች ተሟልቷል ማለት እንደማይቻል እና በመስማት ችግር እና በተግባበቦት ረገድ የሚስተዋሉ መታረም ያለባቸው ጉዳዮች መኖታቸውን ገልጸዋል፡፡

ኮሚሽነር ርግበ አክለውም፤ በሕዝብ ትራንስፖርቶች ላይ የተቀመጡ መስፈርቶች አለመተግበር በተመለከተ ተጠያቂ የሚሆን አካል ባለመኖሩ የአካል ጉዳተኞች መብት እየተከበረ አለመሆኑ ተናግረዋል፡፡

የትራንስፖርት አገልግሎት ለአካል ጉዳተኞች ተደራሽነት በተመለከተ ለኮሚሽኑ ተደጋጋሚ ቅሬታዎች እንደሚቀርቡ የገለጹ ሲሆን፤ በተለይም ለአካል ጉዳተኛ ዜጎች ምቹ ሆነው የተዘጋጁ መወጣጫ ያላቸው የሕዝብ ተሽከርካሪዎች ቢኖሩም አገልግሎት የሚሰጠው በሹፌሮች መልካም ፈቃድ ላይ የተመሰረተ የሚሆንበት አጋጣሚ እንደሚስተዋል ገልጸዋል፡፡

የኮሚሽንኑ የሴቶች፣ ሕጻናት፣ አካል ጉዳተኞች እና አረጋዊያን መብቶች ኮሚሽነር ርግበ ገብረሃዋሪያ አክለውም የግንዛቤ እጥረት በስፋት እንደሚስተዋል ገልጸው፤ በትራንስፖርት ላይ የአካል ጉዳተኞችን መብት ለማስጠበቅ በአገልግሎት አሰጣጡ ላይ ክትትል እና ተጠያቂነት ማስፈን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
#ahaduRadio
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: