ደቡብ ኮሪያ እና አሜሪካ በጋራ ወታደራዊ ልምምዶችን በጀመሩበት በአሁኑ ወቅት ሰሜን ኮሪያ በርካታ የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራዎችን ማድረጓ ተሰምቷል፡፡
ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ወደስልጣን ከመጡ በኋላ ሰሜን ኮሪያ ያደረገችዉ የመጀመሪያዉ የባለስቲክ ሚሳዔል ሙከራ መሆኑም ተገልጿል፡፡
የደቡብ ኮሪያ ጦር እንዳስታወቀው ሰሜን ኮሪያ በዚህ አመት ብቻ ለአምስተኛ ጊዜ የባለስቲክ ሚሳኤል ሙከራ አድርጋለች፡፡
የሰሜን ኮሪያ የሚሳኤል ሙከራ በጋራ ወታደራዊ ልምምድ ማድረግ ለጀመሩት ደቡብ ኮሪያና አሜሪካ መልዕክት ለማስተላለፍ ያለመ ነዉ ተብሏል፡፡
የሁለቱ አገራት የጋራ ወታደራዊ ልምምድ እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር መጋቢት 20 ድረስ እንደሚቀጥል ተገልጿል ሲል የዘገበው አልጀዚራ ነው፡፡
@seledadotio
@seledadotio
Related Posts
- Advertisement -









No comments yet.