#Ethiopia| አክሎክ ሞተርስ በኢትዮጵያ ውስጥ የኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎችን ለማምረት በዝግጅት ላይ መሆኑን ይፋ አደረገ። ኩባንያው ይህን ይፋ ያደረገው ዛሬ መጋቢት 1 ቀን 2017 ዓ.ም በቃሊቲ በሚገኘው ፋብሪካው በሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ነው።
በተጨማሪም አክሎክ ሞተርስ ቀደም ሲል ከተለያዩ ማህበራት ጋር የነበረውን አለመግባባት በሰላም መቋጨቱን አስታውቋል። ቀደም ሲል ለ65 ማህበራት ተሽከርካሪዎችን ለማቅረብ ውል የነበረ ቢሆንም፣ በተፈጠረ አለመግባባት 16 ማህበራት ክስ መስርተው ነበር። ይሁን እንጂ ከእነዚህ ውስጥ ስድስቱ ክሳቸውን በማቋረጥ ከኩባንያው ጋር እርቅ ፈጽመዋል።
በእርቅ ስምምነቱ መሠረት፣ ተሽከርካሪ የሚፈልጉ የማህበሩ አባላት በሦስት ወራት ጊዜ ውስጥ ተሽከርካሪዎቻቸውን እንደሚረከቡ ተገልጿል። እንዲሁም ገንዘባቸውን መመለስ የሚፈልጉ ደንበኞች በ45 ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረግላቸዋል።
የአክሎክ ሞተርስ ሥራ አስኪያጅ አቶ ታመነ ካሳሁን እንደገለጹት ኩባንያው ባለፈው ዓመት 800 ተሽከርካሪዎችን ለደንበኞች ያቀረበ ሲሆን፣ በዚህ በጀት ዓመት ደግሞ 400 ገደማ ተሽከርካሪዎችን ለማስተላለፍ አቅዷል።
አክሎክ ሞተርስ በአዲስ አበባ እና በመቀሌ ከተሞች ተሽከርካሪ መገጣጠሚያ ፋብሪካዎች ያሉት ሲሆን፣ ከ16 በላይ የተለያዩ ሞዴሎችን እየገጣጠመ ለገበያ ያቀርባል። ኩባንያው በተለይም የውሊንግ፣ የባውጅን እና የጂቶር ምርት የሆኑ ተሽከርካሪዎችን በሀገር ውስጥ በመገጣጠም ይታወቃል።
በኤሌክትሪክ ተሽከርካሪዎች ምርት ዙሪያም መንግስት እያደረገ ያለውን ጥረት ለመደገፍ ኩባንያው የውሊንግ የኤሌክትሪክ መኪናዎችን በቅርቡ ወደ ገበያ ለማቅረብ እየሠራ መሆኑን ገልጿል።
አክሎክ ሞተርስ የተሻለ አገልግሎት ለመስጠት የሚያስችለውን ሰፋ ያለ የመገጣጠሚያ ቦታ ለማግኘት ጥያቄ ማቅረቡንም ጨምሮ ገልጿል።
…
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።
“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet
ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26
ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet
ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet
ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet
ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet
አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et
ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et



Source: GetuTemesgen









No comments yet.