ዕለታዊ በረራ ወደ ሞስኮ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | የኢትዮጵያ አየር መንገድ በቅርቡ ወደሞስኮ በየቀኑ በረራ እንደሚጀምር አስታወቀ፡፡ የአየር መንገዱ ቺፍ ኮሜርሺያል ኦፊሰር(ሲሲኦ) አቶ ለማ ያደቻ ሲናገሩ ‹‹የኢትዮጵያ ጂኦግራፊያዊ አቀማመጥ ከሩሲያ እስከ ቻይና በተዘረጋው ብሪክስ መሀል ላይ የሚገኝ ነው፡፡

ስለዚህም የኢትዮጵያ አየር መንገድ በብሪክስ አባል አገራት መካከል ያለው እንቅስቃሴ መልካም እንዲሆን የሚፈልግ ከመሆኑም በላይ በዚህ እድል ተጠቃሚ ለመሆንም እቅድ አለው›› ብለዋል፡፡ ብሪክስ በአባል አገራቱ መካከል የንግድና ኢንቨስትመንት ልውውጥ እንዲሁም የሰዎች ዝውውር እንዲያድግ የሚሰራ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

አቶ ለማ ጨምረውም የብሪክስ አባል አገራት የእርስ በእርስ ግብይትና የሰዎች ዝውውር ሲያድግ ኢትዮጵያም የዚህ አባል እንደመሆኗ መጠን የኢትዮጵያ አየር መንገድም የተሳፋሪዎቹና የጭነት ዝውውሩ እንደሚጨምርለት አስረድተዋል፡፡ በአሁኑ ወቅት አየር መንገዱ በሳምንት አምስት ቀናት ወደሩሲያ ዋና ከተማ ሞስኮ እንደሚበር ጠቅሰውም ይህንን በየቀኑ ለማድረግ ማቀዳቸውን አስረድተዋል፡፡

በሚቀጥለው ጥቅምት ወር ይህንን እለታዊ በረራ ለመጀመር መታቀዱንም አስታውቀው ሩሲያዊያን በአፍሪካ ውስጥ ተደራሽነታቸው እየሰፋ ከመምጣቱ ጋር አየር መንገዱ በዚህ ግንኙነት ትልቁን የትራንስፖርት ሚና እየተጫወተ መሆኑን ማስረዳታቸውን ስፑትኒክ አፍሪካ ዘግቧል፡፡
#zehabesha

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2