ባርሴሎና በሻምፒዮንስ ሊጉ ሩብ ፍጻሜ የገባ የመጀመሪያ ክለብ ሆኗል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ መርሃ ግብር ባርሴሎና ቤኔፊካን በአጠቃላይ ውጤት 4 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።

ማምሻውን በካምፕ ኑ ስታዲየም በተካሄደው የሁለቱ ቡድኖች የመልስ ጨዋታ ባርሴሎና 3 ለ 1 አሸንፏል።

ራፊኒያ ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ላሚን ያማል ቀሪዋን ግብ ለባርሴሎና ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ኒኮላስ ኦታሜንዲ ለቤኔፊካ ብቸኛውን ግብ ከመረብ ጋር አገናኝቷል።

ባርሴሎና በደርሶ መልስ ውጤት 4 ለ 1 በማሸነፍ ሩብ ፍጻሜውን ተቀላቅሏል።

ምሽት 5 ሰዓት ላይ ሊቨርፑል ከፒኤስጂ የሚያደርጉት ጨዋታ በጉጉት ይጠበቃል።

በሌሎች የጥሎ ማለፍ መርሃ ግብሮች ባየር ሌቨርኩሰን ከባየር ሙኒክ እና ኢንተር ሚላን ከፌይኖርድ ሮተርዳም በተመሳሳይ ከምሽቱ 5 ሰዓት ላይ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።
#ena

ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://en.getutemesgen.et





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: