በህሙማን ላይ የወሲብ እና የቁማር ሱስ ያስከተለው መድኃኒትበዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ከቁጥጥር የወጣ የሰውነት እንቅስቃሴ ህመ…

- Advertisement -
Sidebar AD
👀በህሙማን ላይ የወሲብ እና የቁማር ሱስ ያስከተለው መድኃኒት
በዩናይትድ ኪንግደም (ዩኬ) ከቁጥጥር የወጣ የሰውነት እንቅስቃሴ ህመም (movement disorders) የገጠማቸው ሴቶች የተሰጣቸው መድኃኒት ያለው የጎንዮሽ ጉዳት እንዳልተነገራቸው ለቢቢሲ ገለጹ።
ሕክምና ከወሰዱ መካከል 20 ሴቶች ለቢቢሲ እንደገለጹት የተሰጣቸው መድኃኒት “አሉታዊ ወሲባዊ ባህሪ” እንዲያዳብሩ የሚያደርግ መሆኑ አልተነገራቸውም።
መድኃኒቱ ሕይወታቸውን እንዳመሳቀለውም ተናግረዋል።
እንደ ሌሎቹ ሴቶች በእርግዝና ወቅት ከቁጥጥር የወጣ የሰውነት እንቅስቃሴ የገጠማት ክሌር እንቅልፍ አጥታ እና ከቆዳዋ ሥር በሚሰማት ህመም እየተሰቃየች እንደነበር ተናግራለች።
ከወለደች በኋላም ህመሙ ሲቀጥል ሮፒኒሮል የተባለ መድኃኒት ታዘዘላት። የጎንዮሽ ጉዳቱ በሐኪም አልተነገራትም ነበር። ህመሙ ከቆመ ከዓመት በኋላ የወሲብ ፍላጎቷ ላይ ከፍተኛ ለውጥ አስተዋለች።
ያጋጠማትንም ሁኔታ “በጣም ወጣ ያለ ብዬ ነው ስሜቱን ልገልጸው የምችለው” ትላለች።
ጠዋት ከቤቷ ወጥታ ወሲብ ለመፈጸም ስትሞክር ትውል ነበር።
አለባበሷም ሰውነትን የሚያጋልጥ ልብስ ሆኖ ነበር። የትኛውንም ወንድ ስታይ ሰውነቷን አጋልጣ ታሳይ እንደነበር ትናገራለች።
የትዳር አጋር ቢኖራትም ባህሪውን ከማሳየት ራሷን ማስቆም አልቻለችም።
ያጋጠማትን ያልተለመደ ባህሪ ከመድኃኒቱ ጋር ለማስተሳሰር ዓመታት ወስዶባታል። መድኃኒቱን መውሰድ ስታቆም ባህሪውም ጠፋ።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: