አርቲስት አንዱአለም ጎሳ በቀነኒ ሞት ተጠርጥሮ ፍርድ ቤት ቀረበ

- Advertisement -
Sidebar AD

አርቲስት አንዱአለም ጎሳ በእጮኛው ቀነኒ አዱኛ ሞት ተጠርጥሮ ከታሰረ ከሁለት ቀናት በኋላ ፍርድ ቤት መቅረቡን ጠበቃው ለቢቢሲ አፋን ኦሮሞ ገልጿል።

ፖሊስ እስካሁን አሻራ ማንሳቱን፣ አስከሬኑን ወደ ሆስፒታል በመላክ፣ የአስከሬን ምርመራ ማድረጉን ገልጾ የሰው ማስረጃዎችን በማሰባሰብ ላይ እንደሚገኝ ተናግሯል።

አሁን ፎቶግራፎችን ከመዝገቡ ጋር ለማያያዝ፣ የሰዎች ምስክርነት ለመስጠት እና የአስከሬን ምርመራው እስኪመጣ ድረስ ለማጣራት 14 ቀናት ያስፈልገኛል ብሏል።

የአንዱአለም ጠበቃ በበኩሉ የዋስ መብት ይሰጥ ብሎ ቢጠይቅም ፍርድ ቤት የአስክሬን ምርመራ እንስኪደርስ በማለት 13 ቀናት ድምፃዊው በማረሚያ ቤት እንዲቆይ ወስኗል።



Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2