“የፌደራል መንግስቱ ጣልቃ እንዲገባ ያቀረብነው ጥያቄ የለም” አሉ አቶ ጌታቸው ረዳ፡፡የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳ…

- Advertisement -
Sidebar AD
☄️“የፌደራል መንግስቱ ጣልቃ እንዲገባ ያቀረብነው ጥያቄ የለም” አሉ አቶ ጌታቸው ረዳ፡፡
የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ይህንን ያሉት በአዲስ አበባ ለመገናኛ ብዙሃን እየሰጡት ባለው መግለጫ ነው፡፡
“የፌደራል መንግስን ጣልቃ እንዲገባ የሚጠይቅ ምክር ቤትም የለም የሚያስችልም ቁመና የለም” ሲሉም ገልጸዋል፡፡
አቶ ጌታቸው “ፌደራል መንግስቱ ክልሉ ስጋት ላይ ነው ብሎ ካመነ ግን የእኛን ጥያቄ መጠበቅ አያስፍልገውም ብለዋል”፡፡
በትግራይ ከፖሊስ በላይ የታጠቀ ሰራዊት ነው ያለው የሚሉት አቶ ጌታቸው “ይህንን ለማስቆም ደግሞ ፌድራል መንግስት ገብቶ ማረጋጋት የሚያስችል ስልጣን አለው ” ብለዋል፡፡
ጊዜያዊ አስተዳደሩ የፌደራል መንግስቱ የፕሪቶሪያውን ስምምነት ተከትሎ ክልሉ ችግር ላይ ነው ብሎ ስላሰበ መግባትን ምርጫው ማድረግ ይችላል ብለዋል፡፡
“በካቢኔ ደረጃ ተሰብስብን የፌደራል መንግስቱ ወደ ትግራይ ይግባ ብለን አልጠየቅንም መጠየቅም አያስፈልገንም” ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በአሁን ሰዓት አዲስ አበባ ሸራተን አዲስ ሆነው ስለ ክልሉ ሁኔታ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ናቸው።
የእና ፍላጎት ጦርነትን ማስወገድ ነው የፌድራል መነግስቱም ይህንን ነው ሚፈልገው ሲሉም ተናግረዋል፡፡
ፕሬዝዳንቱ በአሁን ሰዓት ስለ ክልሉ ሁኔታ ጋዜጣዊ መግለጫ እየሰጡ ሲሆን ሌሎች የሚነሱ ጠያቄዎችን ጣቢያችን ተከታትሎ የሚያቀርብ ይሆናል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: