Man of the match

- Advertisement -
Sidebar AD

በዩሮፓ ሊግ ማንቸስተር ዩናይትድ እና ቶተንሃም ሆትስፐር ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቀሉ

#Ethiopia | በዩሮፓ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ የእንግሊዙ ማንቸስተር ዩናይትድ የስፔኑን ክለብ ሪያል ሶሲዳድን በድምር ውጤት 5 ለ 2 በማሸነፍ ለሩብ ፍፃሜው አልፏል።

በሪያል ሶሲዳድ ሜዳ አንድ አቻ ወጥተው የነበሩት ቀያይ ሴይጣኖቹ ዛሬ በሜዳቸው ያደረጉትን ጨዋታ 4 ለ 1 አሸንፈዋል።

የማሸነፊያ ግቦቹንም ብሩኖ ፈርናንዴዝ (3) እና ዲያጎ ዳሎት 1 ሲያስቆጥሩ የሪያል ሶሲዳድን የማስተዛዘኛ ግብ ኦያርዛባል አስቆጥሯል።

በዛሬው ጨዋታ ሁለት ፍፁም ቅጣት ምቶችን ያስቆጠረው የማንቸስተር ዩናይትዱ አማካይ ተጫዋች ብሩኖ ፈርናንዴዝ በዩሮፓ ሊግ ታሪክ አስር የፍፁም ቅጣት ምቶችን በማስቆጠር በርካታ ፍፁም ቅጣት ምት ያስቆጠረ ተጨዋች መሆን መቻሉ ተገልጿል።

በመጀመሪያው ጨዋታ 1 ለ 0 ተሸንፎ የነበረው ቶተንሃም ሆትስፐር በበኩሉ በዛሬው ጨዋታ አልካማርን 3 ለ 1 በማሸነፉ 3 ለ 2 በሆነ ድምር ውጤት ሩብ ፍፃሜውን መቀላቀል ችሏል።

በሌሎች የዩሮፓ ሊግ ጨዋታዎች፣ አትሌቲክ ቢልባኦ ሮማን በድምር ውጤት 4 ለ 3፣ ኢንትራች ፍራንክፈርት አያክስን 6 ለ 2፣ ላዚዮ ቪክቶሪያ ፒዘንን 3 ለ 2፣ ቦዶኤ/ግሊምፕት ኦሊምፒያኮስን 4 ለ 2 እንዲሁም ሊዮን ኤፍሲኤስቢን 7 ለ 1 በድምር ውጤት በማሸነፍ ወደ ሩብ ፍፃሜው ያለፉ ቡድኖች ናቸው።

ቼልሲ በበኩሉ በአውሮፓ ኮንፈረንስ ሊግ የጥሎ ማለፍ የመልስ ጨዋታ ኮቤንሀቨንን 1 ለ 0 አሸንፏል። በድምር ውጤትም 3ለ1 በማሸነፍ ሩብ ፍፃሜውን ተቀላቅሏል።





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1