#Ethiopia | በሳዑዲ ዓረቢያ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የነበሩ 961 ኢትዮጵያውያን በዛሬው ዕለት ወደ ሀገራቸው መመለሳቸውን የሴቶችና ማሕበራዊ ጉዳዮች ሚኒስቴር ገለጸ።
በዛሬው ዕለት በተደረገ 3 ዙር በረራ የተመለሱት 578 ወንዶች፣ 336 ሴቶች እና 47 ጨቅላ ህፃናት ሲሆኑ፤ ከተመላሾች መካከል 48 ያህል እድሜያቸው ከአስራ ስምንት ዓመት በታች የሆኑ ታዳጊዎችም ይገኙበታል ተብሏል።
በ4ኛው ዙር በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ የሚገኙ 50 ሺህ ዜጎችን ወደ ሀገራቸው ለመመለስ ታቅዶ ከመጋቢት 3/ 2017 ዓ.ም ጀምሮ በይፋ መጀመሩ ይታወቃል። በዚህም እስካሁን 1 ሺህ 961 ኢትዮጵያውያንን ወደ ሀገር መመለስ መቻሉ ተገልጿል።
ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ከሚመለከታቸው ባለድርሻና አጋር አካላት ጋር በመቀናጀት ለተመላሽ ዜጎች በአየር ማረፊያና በማቆያ ማዕከላት ተገቢውን ድጋፍ እና እንክብካቤ የማድረግ እና ከቤተሰብ ጋር የማቀላቀል ስራም እየሰራ መሆኑንም አስታውቋል።
Source: GetuTemesgen









No comments yet.