በእስራኤል ወታደሮች የተገደሉት ኢትዮጵያውያን የእስራኤል ወታደሮች፣ ትናንት ከዮርዳኖስ አቋርጠው ወደ እስራኤል የገቡ ሁለት ኢ…

- Advertisement -
Sidebar AD
☄️በእስራኤል ወታደሮች የተገደሉት ኢትዮጵያውያን
የእስራኤል ወታደሮች፣ ትናንት ከዮርዳኖስ አቋርጠው ወደ እስራኤል የገቡ ሁለት ኢትዮጵያዊያንና አንድ ኡጋንዳዊ ተኩሰው መግደላቸውን የአገሪቱ የዜና ምንጮች ዘግበዋል።
ወታደሮቹ የተሠጣቸው ትዕዛዝ የማስጠንቀቂያ ተኩስ እንዲተኩሱ እንደነበር ዘገባዎቹ አመልክተዋል።
በርካታ ጥገኝነት ጠያቂዎችና የሕገወጥ ሰዎች ዝውውር ሰለባዎች ከዮርዳኖስ ወደ እስራኤል እንደሚገቡና ድንበር ጠባቂ ወታደሮች እንዲመልሷቸው ሥልጣን እንደተሠጣቸው ዘገባዎቹ ጠቅሰዋል።
ወታደሮቹ ግድያውን የፈጸሙት፣ ማቾቹ “ስጋት የሚደቅን” እንቅስቃሴ በማድረጋቸው እንደኾነ የአገሪቱ መከላከያ ባለሥልጣናት ተናግረዋል ተብሏል።
አንድ ኢትዮጵያዊን ጨምሮ አምስት የውጭ ዜጎች ደሞ ታስረው ወደ ዮርዳኖስ እንዲመለሱ እንደተደረጉ ተገልጧል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: