#ብርሃን የገለጸልን ቀዳሚው መምህራችን

- Advertisement -
Sidebar AD

አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን በሦስተኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ሕዳር 26 245 ዓ.ም ከአባቱ ቅዱስ ምናጦስና ከእናቱ ቅድስት ማርያም ሰናይት በጢሮስ /ግሪክ/ ተወለደ። የመጀመሪያ ስሙ ፍሬምናጦስ ነበር። የ12 ዓመት ልጅ እያለ ሜሮጵዮስ የተባለ ፈላስፋና ነጋዴ ይዞት ወደ ሀገራችን መጣ። ኤድስዮስ የተባለ ሰውም አብሮት እንደነበረ ይታወቃል። እነዚህን ሁለት ወጣቶች አስከትሎ የመጣው ሜሮጵዮስ በቀይ ባሕር አካባቢ ይኖሩ የነበሩ ሰዎች በጣሉበት አደጋ ሲሞት ፍሬምናጦስና ኤድስዮስ በወቅቱ የአክሱም ንጉሥ ከነበረው ታዜር ጋር አድገዋል። ንጉሡ በአእምሮ መብሰላቸውን ተመልክቶ ፍሬምናጦስ በጅሮንድ ኤድስዮስን ጋሻ ጃግሬው አድርጎ ሾማቸው። ከዚያ በኋላ ንጉሥ ታዜር ሲያርፍ ወደ ፈለጉበት እንድሄዱ ነፃ ስለተለቀቁ ኤድስዮስ ወደ አገሩ ተመልሶ ሄዷል።

አባታችን አቡነ ሰላማ ከሳቴ ብርሃን ግን በጨለማ የሚኖረውን ሕዝብ ትቼ ወደ አገሬ አልመለስም በማለት እኛን በማፍቀር እንደቀረ ታሪክ ያስረዳናል። በጊዜው በሀገራችን ስርዓተ ንስሐ፣ ስርዓተ ጥምቀት፣ ስርዓተ ቅዳሴ፣ ስርዓተ ቅዱስ ቁርባን የሚያከናውን ጳጳስ ስላልነበረ ነገስታቱ ኢዛናና ሳይዛና ጵጵስና እንዲያመጣ አባታችንን ወደ ግብጽ ላኩት። በግብጽም ስርዓቶቹን በመማር በቅዱስ አትናትዮስ አንብሮተ እድ ˝ኤጲስ ቆጶስ ዘአክሱም ወዘኩላ ኢትዮጵያ” ተብሎ ጵጵስና ተቀበለ። ከተመለሰ በኋላም መጀመሪያ ነገስታት ኢዛናና ሳይዛናን አጥምቆና አቁርቦ አብርሃ ወአጽበሃ በማለት ስመ ክርስትና ሰጣቸው። በመቀጠልም በመላው አገራችን እየተዘዋወረ በማስተማር ስርዓቱን ፈጽሟል። ከዚህም የተነሳ ጨለማን አስወግዶ ብርሃንን የገለጠ ቀዳሚ የምድረ ሐበሻ ታላቅ ሐዋርያ ነው። የቀናች ሃይማኖትን በማስተማር ጨለማውን ብርሃን በማድረጉ “ብርሃን ገላጭ ሰላማ” ተብሏል።

አባታችን በኢትዮጵያና ኤርትራ በኪደተ እግሩ ተመላለሶ ወንጌል አስተምሯል፣ እልፍ ድውያንን ፈውሶ ሙታንን አስነስቷል ይላል ገድሉ። ባዕድ አምልኮ ያመልክ የነበረውን ሕዝብም በስብከቱ እግዚአብሔርን ወደ ማመን መልሶታል። በጸሎቱ አጋንንትን ጠራርጎ ከአገራችን በማስወጣት ሰላም የሰጠን የሰላም አባት ነው። በ350 ዓ.ም ክርስትና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሃይማኖት ሆኖ እንዲታወጅ አድርጓል። ለዚህም ነው አባታችን ቅዱስ ያሬድ “ዝንቱ ብእሲ መምህርነ ዘተፈነወ ውስተ ምድርነ ይክስተ ብርሃነ” በማለት አመስግኖታል። ብርሃንን ለመግለጥ ወደ አገራችን የተላከ መምህራችን ማለቱ ነው። ከሰራቸው የተለያዩ ድንቅ ሥራዎች ውስጥም ወንጌል የሚያስተምሩና የሚያጠምቁ የሚያቆርቡ ካህናትና ዲያቆናት ሾመ፡፡

ምእመናን መካሪ የንስሐ አባት እንዲኖራቸው አድርጓል፣ ከአብርሃ ወአጽብሃ ጋር በመሆን አብያተ ክርስቲያን አንጸዋል፣ ቅዱሳት መጻሕፍት ከሱርስት፣ እብራይስጥና ከግሪክ ወደ ግእዝ ቋንቋ እንዲተረጎሙ አድርጓል፣ የሳባውያንን ፊደል አቀማመጥ በማስተካከል ከግራ ወደ ቀኝ የመጻፍንና የማንበብን ዘዴ በማስተማር ብዙ ውለታ የዋለልን ታላቅ አባት ነው። ይህ ታላቅ ኣባት በሀገራችን የወንጌልን ፋና ያበራ መንበረ ጵጵስናን ያስገኘልንና ስርዓተ ቤተክርስቲያን የወጠነልን፣ ለ150 ዓመታት እንደ ሻማ ቀልጦ ለእኛ ብርሃን የሰጠን ታላቅ ባለውለታ የሀገራችን ቀዳሚ ሐዋርያ ነው፡፡

በገዳማዊ ኑሮ ያሉትን እየረዳንና በዓታቸውን እያጸናን የበረከታቸው ተሳታፊ እንሁን፡፡

ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም

ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391

ወይም

አቢሲኒያ ባንክ
141029444

የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2