በኢትዮጵያ የሚገኙ የቤት ሠራተኞችን የሙያ ስልጠና በመስጠትና የብቃት ምዘና ፈተና (COC) እንዲወስዱ ለማድረግ እየተሰራበት እንደሚገኝ ተገለጸ
#Ethiopia | የቤት ውስጥ ሠራተኞች ራሳቸውን በሙያ ብቁ የሚያደርጉበት ስልጠና በመስጠትና የሙያ ብቃታቸውን የሚመዝን ፈተና (COC) እንዲወስዱ ለማድረግ እየተሰራበት እንደሚገኝ አንድነት ኢትዮጵያ የቤት ውስጥ ሠራተኞች ማኅበራት ሕብረት አስታውቋል፡፡
የቤት ሠራተኞች በማኅበር ከመደራጀት በዘለለ ስልታዊ የሆነ የሙያ ክህሎታቸውንና ደረጃቸውን ሊመዝኑ የሚችሉ ተቋማቶች በሀገር አቀፍ ደረጃ መኖራቸውን የሕብረቱ ፕሬዝዳንት ሂሩት አበራ ለአሐዱ ገልጸዋል።
በመሆኑም በሥራና ክህሎት በኩል ተግባራዊ በሚደረገው አሰራር መሠረት ማንኛውም ሰው መሠረታዊ የሆኑ ምዘናዎችን በመውሰድ ራሱን ብቁ ማድረግ የሚችልበት አግባብ በመኖሩ፤ የቤት ሠራተኞችም የትምህርት ደረጃቸው ሳይፈለግ በሙያቸው ብቻ ብቁ መሆናቸውን የሚያረጋግጡበት ምዘና ስለመኖሩ አስታውቀዋል።
በዚህም መሠረት ለሙያው ብቁ መሆናቸውን የሚያረጋግጥ የብቃት ምዘና (COC) እንዲወስዱ ለማድረግ ማኅበሩ እገዛ እያደረገ እንደሚገኝ ገልጸዋል።
“ከዚህ ጎን ለጎንም ራሳቸውን አብቅተውና የመደራደር አቅማቸውን ጨምረው ከአሠሪዎቻቸው ጋር የሚችሉትን ሙያ በማሳየት ብቁ ከሆኑ በሙያቸውና በምዘናቸው መሠረት የሚቀጠሩበትን መንገድ ለማመቻቸትም እየተሰራበት ይገኛል” ብለዋል።
የሙያ ብቃት ምዘናውን (COC) ማንኛውም ‘በሙያዬ ብቁ ነኝ’ ያለ ሰው ምዘናው በሚሰጥበት ተቋም ውስጥ መፈተን የሚችል ሲሆን ስልጠና የሚያስፈልጋቸው ደግሞ ከአንድ ወር ከግማሽ እስከ 6 ወር በሚደርሱ አጫጭር ስልጠናዎች መሰረት ራሳቸውን ማብቃት እንደሚችሉ ተናግረዋል።
ከዚህ ባሻገርም በኢትዮጵያ ለቤት ሠራተኞች ትምህርትና ስልጠና እንዲሁም ሙሉ ጊዜ ገብተው መሰልጠን የሚፈልጉ የቤት ሠራተኞችን በተመለከተም በዛ ልክ የተዘጋጀ ፖሊሲ ባለመኖሩ ስርዓተ ትምህርቱ ላይ ማስተካከያዎች እንዲደረጉ ከትምህርትና ስልጠና ተቋማት ጋራ እየተሰራበት እንደሚገኝ አስታውቀዋል።
በመሆኑም የቤት ሠራተኞች የሙያ ብቃታቸውን እንዲያሳድጉ ለማድረግ የተለያዩ ስልጠናዎችና ግንዛቤዎች እየተሰጡ እንደሚገኙ ገልጸዋል።
አሐዱ ከዚህ ቀደም የቤት ሠራተኞች የጡረታ ተጠቃሚ የሚሆኑበትን አግባብ ጨምሮ ማህበራዊ ዋስትናቸውን የሚያረጋግጥ የሥራ ቅጥር ውልና አጠቃላይ ደንብ በ6 ወር ውስጥ ይፀድቃል መባሉን መዘገቡ ይታወሳል።
#ahaduRadio
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ ቤተሰብ ይሁኑ።
“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet
ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26
ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet
ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet
ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet
ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet
ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et
አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et
Source: GetuTemesgen









No comments yet.