ከዛሬ ሚያዝያ 30 ቀን 2017 ዓ.ም ከምሽቱ 12 ሰዓት ጀምሮ በሥራ ላይ የሚቆይ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ጭማሪ መደረጉን፤ የንግድና ቀጠናዊ ትስስር ሚኒስቴር አስታውቋል።
በዚህም መሠረት፦
👉 አንድ ሊትር ቤንዚን 122 ብር ከ53 ሳንቲም
👉 አንድ ሊትር ኬሮሲን 116 ብር ከ49 ሳንቲም
👉 አንድ ሊትር ነጭ ናፍጣ 116 ብር ከ49 ሳንቲም
👉 አንድ ሊትር ቀላል ጥቁር ናፍጣ 106 ብር ከ77 ሳንቲም
👉 አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 104 ብር ከ08 ሳንቲም
👉 አንድ ሊትር የአውሮፕላን ነዳጅ 109 ብር ከ56 ሳንቲም እንዲሸጥ መወሰኑን አሐዱ ያገኘው መረጃ አመላክቷል።
በዚህም የቀላል ጥቁር ናፍጣ የሊትር መሸጫ ዋጋ 109 ብር 22 ሳንቲ የነበረ ሲሆን፤ የ3 ብር ከ55 ሳንቲም ቅናሽ ማሳየቱን ለማወቅ ተችሏል።
በተጨማሪም አንድ ሊትር ከባድ ጥቁር ናፍጣ 106 ብር ከ75 ሳንቲም ከነበረበት 106 ብር ከ77 ሳንቲም ዝቅ ያለ ሲሆን፤ የአውሮፕላን ነዳጅም 113 ብር ከ20 ሳንቲም ከነበረበት ወደ 109 ብር ከ56 ሳንቲም ዝቅ ማለቱ ታውቋል።
Source: FastMereja









No comments yet.