#Ethiopia | የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከፍተኛ ዝግጅት ሲያደርግበት የቆየውና በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው 42ኛው የሻምበል አበበ ቢቂላ የማራቶን ውድድር በሲዳማ ክልል ርዕሰ መዲና ሐዋሳ ከተማ ተካሂዷል።
በዚሁ ታላቅ የስፖርት መድረክ ላይ ከ300 በላይ አትሌቶች የተሳተፉ ሲሆን ከእነዚህም ውስጥ 74ቱ ሴቶች እንዲሁም 249ኙ ወንዶች መሆናቸው ታውቋል።
ውድድሩን ይበልጥ ሳቢ ካደረጉት ሁኔታዎች መካከል 12 ታዋቂ ክለቦች እና 4 ክልሎች በንቃት በመሳተፍ ያሳዩት ብርቱ ፉክክር ዋናው መገለጫ ነበር።
የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ከሲዳማ ክልል አትሌቲክስ ፌዴሬሽን ጋር በመተባበር የቴክኒክና የልኬት ሥራዎችን በጥራት አጠናቆ ለውድድሩ ስኬት ከፍተኛ ርብርብ ማድረጉን የፌድሬሽኑ ከፍተኛ የውድድር ባለሙያ ገልጸዋል እንደነበር ይታወሳል።
ፌዴሬሽን ለአጠቃላይ ውድድሩ ማከናወኛ የሚሆን 6 ሚሊዮን ብር በጀት የመደበ ሲሆን ከዚህ ውስጥ 458 ሺህ ብሩ በቀጥታ ለአሸናፊዎች ሽልማት እንዲውል ተደርጓል።
ውድድሩ በወንዶች በሴቶች እንዲሁም ዕድሜያቸው ከ50 ዓመት በላይ በሆኑ አንጋፋ አትሌቶች መካከል የተካሄደ ሲሆን በዕለቱ የተመዘገቡት የውድድሩ የመጨረሻ በወንዶች እና ሴቶች መደብ የተመዘገበው ውጤት፦
በወንዶች ማራቶን ፉክክር፦
1ኛ፦ ገመቹ ያደሳ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)
2ኛ፦ ባንቱ መኮንን (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)
3ኛ፦ አቡ ገለቱ (መቻል ስፖርት ክለብ)
በሴቶች ማራቶን ፉክክር፦
1,አትሌት ጠጅቱ ስዩም (ከመቻል)
2,አትሌት ከረኒ ጀሊሳ (ከኦሮሚያ ፖሊስ)
3,አትሌት ትዕግስት ጌትነት (ከኢትዮ ኤሌክትሪክ)
በዚህም መሠረት በሁለቱም ጾታዎች ከአንደኛ እስከ ስምንተኛ ደረጃን ይዘው ላጠናቀቁ አትሌቶች እንደየደረጃቸው ከ10 ሺህ እስከ 50 ሺህ ብር የሚደርስ ማበረታቻ የገንዘብ ሽልማት ተበርክቶላቸዋል።
በአንጋፋ (ቬትራን – ከ50 ዓመት በላይ) አትሌቶች ዘርፍ፦
1ኛ፦ በቀሉ ረታ
2ኛ፦ ቦጋለ ሰይፉ
3ኛ፦ አሰፋ መገርሳ ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ውድድሩን አጠናቀዋል።
ለ Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን) ሚዲያና ኮሙዩኒኬሽንስ
ያፌት ገ/ህይወት
ከሲዳማ ፤ ሐዋሳ



Source: GetuTemesgen









No comments yet.