በእድሜ ያልተገደበ የቀለም ጉዞ

- Advertisement -
Sidebar AD

* ድንቅ ቁጪት ከTTI…እስከ- 2-PHD*(2-ዶክትሬት ) ውጤታማ ዕድሜ

#Ethiopia | ዶ/ር ማናዬ አበራ ሸመሎ ይባላሉ ከምሁራን መፍለቂያ አምባ፣ ከከምባቶች እናት አብራክ የተገኙ ፣ በስንዴ ምርቷ ከምትታወቅ ከከምባታዋ ዶዮገና የበቀሉ ድንቅ ቀለሜ ናቸው ።

ስለ አካዳሚክ ቅድመ ታሪካቸው የመጀመሪያ TTI ከደብረብርሃን መምህራን ማሰልጠኛ፣ ድፕሎማቻውን ከሀዋሳ መምህራን ማስልጠኛ ኮሌጅ፣ የመጀመሪያ ድግሪያቸውን ከድላ ዩኒቨርስቲ፣ 2ኛ ድግሪያቸውን ከአንጋፋው አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ተቀብለዋል፤ ለትምህርት ካላቸው ቁጭት የተነሳ 1ኛውን PHD (Philosophy of Higher Diploma) በትምህርት ዕቅድና አመራር ደቡብ አፍሪካ ከሚገኘው ዩኒቨርስቲ አግኝተዋል።

ዶ/ር ማናዬ መቼ በዛው አበቁና ዛሬ ደግሞ 2ኛውን ዶክተሬት ድግሪያቸውን ከአዲስአበባ ራስ ገዝ ዩኒቨርስቲ በትምህርት አመራር በስኬት አጠናቀው ተመርቀዋል ።

የዶክተር ማናዬ አበራ የቁጭት ጉዞ በድል ማጠናቀቅ የመጀመሪያው በትምህርት ሥርዓት ውስጥ ለሀገራችን ብዙ አበርክቶ ያበረከቱ መሆናቸውን ብቻ ሰይሆን ለአዲሱ ትውልድ የጥንካሬ ተምሳሌትም ናቸው።

የዶ/ር ማናዬ ህይወት ጉዞ ለብዙዎቻችን እጅግ አስተማሪ ጉዞ ስሆን ለዚህ ድንቅ ቀን እና ድንቅ ደረጃ በመብቃትዎ እንኳን ደስ አልዎ !! ለማለት እፈልጋለሁ !!

Congratulations ❤❤❤
Ambaye Aberra




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: