የአርሰናል የክረምት የዝውውር መስኮት የመጀመሪያ ፈራሚ ማርቲን ዙቢሜንዲ መሆኑ ተረጋግጧል

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ዙቢሜንዲ ወደ አርሰናል 99.9 በመቶ የተረጋገጠ የዝውውር መረጃ መሆኑ Tbr football መዘገቡ የሚታወስ ሲሆን ተጫዋቹ አሁን ሙሉ ለሙሉ መድፈኞቹን ለመቀላቀል ከስምምነት ላይ ስለመድረሱ ለማወቅ ተችሏል።

ሚኬል አርቴታ ለሁለት አመት ገደማ ሲመኘው የነበረው ዝውውር ከዚህ በኋላ የሚስተጓጎልበት እድል ጠባብ መሆኑ እና ሁለቱ የሳን ሳባስቲያን ተወላጅ ግለሰቦች ኤምሬትስ ላይ እንደሚጣመሩ በስፋት እየተዘገበ ይገኛል።

የስፓንያርዱ አሰልጣኝ ሚኬል አርቴታ Trust the process ፕሮጀክት እነሆ 6ኛ አመቱ ላይ ይገኛል። ተስፋ ሰጪ ነገሮች ቢኖሩም ቡድኑ ግን በትልቁ ሊነሳ የሚችል የዋንጫ ክብር ማሳካት አልቻለም ፤ ታዲያ አሰልጣኙ ያንን ነገር ለማበርከት ዚቢሜንዲ ወሳኝነት ያለው ሚና ይጫወታል የሚል እምነት አለው።

ተጫዋቹ ከሜዳ ውጪ የጠየቃቸው መስፈርቶች ነበሩ ክለቡም ያን አሟልቶ በመገኘቱ ከተጫዋቹ ጋር ከስምምነት ላይ ደርሰዋል የተባለ ሲሆን ከክለቡ ሪያል ሶሲዳድ ጋር በተጫዋቹ ሂሳብ ጉዳይ ማለትም 60 ሚሊዮን ዩሮ የውል ማፍረሻ አለው እና አርሰናል የአከፋፈል ሂደቱን በተመለከተ አቅጣጫ እያስቀመጡ እንደሚገኙ እና ተነጋግረው ከስምምንት ላይ የመድረሳቸው ተገልጿል።

ተጫዋቹን ለማስፈረም ሪያል ማድሪድ ፤ ሲቲ እና ሊቨርፑል ከፍተኛ ጥረት ቢያደርጉም ተጫዋቹ የሚኬል አርቴታን ፕሮጀክት በመቀበል ፤ እንዲሁም ጓደኛው እና የብሄራዊ ቡድን አጋሮቹ ሚኬል ሜሪኖ እና ግብ ጠባቂው ዴቪድ ሬያን ጨምሮ ከኬረን ቲርኒ እና ማርቲን ዙቢሜንዲ ጋር አብሮ ተጫውቷል።

ስለዚህ ሰሜን ለንደን አርሰናል ውስጥ ተጫዋቹ እንግዳ ሳይሆን ቤተኛ እንደሚሆን ይገመታል። በተጫዋቹ ጉዳይ ተስፋ የቆረጡት ሲቲዎች ኒኮ ጎንዛሌዝን ሲያስፈርሙ ፤ ሊቨርፑልም አዲስ የአማካኝ መስመር ተጫዋች ለማስፈረም ገበያውን ያማትራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

የ26 አመቱ ስፔናዊ አማካኝ መስመር ተጫዋች በተጠናቀቀው የውድድር ዘመን ኳስ በማስጣል ፤ የሶሲዳድ የተከላካይ መስመር ላይ ጫና እንዳይኖር በማድረግ ሂደት ላይ አይተኬ የሚባል አይነት ሚናን ለኢማኖል አልጉዋሲሉ ቡድን ሲወጡ ከነበሩ ተጫዋቾች መካከል በዋናነት ስሙ ይጠቀሳል።

ዴክላን ሳይስ ባሳለፍነው የውድድር ዘመን 7 ጎል ሲያስቆጥር 8 ኳስ አመቻችቶ ማቀበል ችሏል። በ8 ቁጥር ወይም ከሳጥን እስከ ሳጥን በመሄድ የቡድኑን የማጥቃት እንቅስቃሴ በነፃነት እንዲያግዝ የዙቢሜንዲ መኖር ከፍተኛ ሚና ይኖረዋል። ለዛም ነው አርሰናል ተጫዋቹን በጥብቅ ለማስፈረም ጥረት እያደረገ የሚገኘው።

ታዲያ እንደ Tbr football በጋዜጠኛው ዳርመሽ አማካኝነት እንደዘገበው ከሆነ መድፈኞቹ ለዚህ ዝውውር ወደ 50 ሚሊዮን ፓውንድ ወይም 61 ሚሊዮን ዩሮ የውል ማፍረሻውን የሚከፍሉ ሲሆን ተጫዋቹም በቃል ደረጃ ወደ ሰሜን ለንደን ለማምራት ከስምምነት ላይ ደርሷል ሲል ዘግቧል።

አምና ይኸው ገንዘብ በሊቨርፑል አማካኝነት የቀረበ ቢሆንም ሶሲዳድም ገንዘቡን ተቀብሎ ተጫዋቹ ወደ መርሲሳይድ አቀና ሲባል 11ኛው ሰአት ላይ ሀሳቡን በመቀየር ዝውውሩን ማከናወን እንደማይፈልግ በማሳወቁ ዝውውሩ ሳይከናወን ቀርቷል።

አሁን ግን ተጫዋቹ የአርሰናል የመጪው የክረምት ዝውውር መስኮት የመጀመሪያ ፈራሚ እንደሚሆን ተረጋግጧል።
#menahriaFm
ባሉበት ሆነው ትኩስ እና ወቅታዊ መረጃዎችን ለማግኝት ከስር ያሉትን ሊንኮች በመጫን ቤተሰብ ይሁኑ።

“””””””””””***””””””””””
ዩቲዩብ ገጽ: https://www.youtube.com/@getutemesgenet

ፌስቡክ ገጽ: https://web.facebook.com/getu26

ቴሌግራም ገጽ: https://t.me/getutemesgenet

ቲክቶክ ገጽ: https://www.tiktok.com/@getutemesgenet

ኢንስታግራም ገጽ: https://www.instagram.com/getutemesgenet

ኤክስ: https://x.com/getutemesgenet

ኢንግሊዘኛ ድረ-ገጽ: https://getutemesgen.et

አማርኛ ድረ-ገጽ: https://amharic.getutemesgen.et



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: