#የታሪክ_እፍታ

- Advertisement -
Sidebar AD

ግንቦት 13 / 1983

#Ethiopia | ከ34 አመት በፊት ልክ በዛሬዋ ዕለት የቀድሞ የኢትዮጵያ መሪ ሌተና ኮሎኔል መንግሥቱ ኃይለማርያም ሃገር ጥለው የሄዱበት ቀን ነው።

17 አመት በሰሜን በኤርትራ እና ትግራይ የተጀመረው የትጥቅ ትግል አድማሱን አስፍቶ፣ግዙፉ አብዮታዊ ሰራዊት ተደርምሶ አማጺያን ወደ አዲስ አበባ በተቃረቡበት የግንቦት ወር መጀመሪያ 1983 ዓ.ም ዳግማዊ ቴዎድሮስ ሲባልላቸው የነበሩት ፕሬዚዳንት ኮበለሉ ተባለ።

ማክሰኞ ግንቦት 13 ቀን 1983 ዓ.ም ብላቴ ወታደራዊ ማሰልጠኛን እጎበኛለሁ ያሉት መንግሥቱ የአውሮፕላናቸውን አቅጣጫ ቀይረው ኬንያ በመግባት በፕሬዚዳንት አራፕ ሞይ እገዛ ወደ ዚምባብዌ ተሻገሩ።

እስከ ግንቦት 13 የኢትዮጵያ ሕዝባዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ፕሬዚዳንት፣የኢሠፓ ማዕከላዊ ኮሚቴ ዋና ጸሃፊ እና የአብዮታዊ ጦር ሃይሎች ዋና አዛዥ የነበሩት መንግሥቱ ስደተኛ ሆኑ።

የ88 አመት አዛውንቱ ሌተና ኮሎኔል መንግስቱ በአሁኑ ጊዜ ኑሯቸውን በዚምባብዌ ጋን ሂል የመኖሪያ መንደር አድርገዋል።
#Nbc_Ethiopia



Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1