” እናቴ ‘ ልጅሽ ሞቷል ‘ ተብላ እያለቀሰች ነበር ፤ ነገር ግን ቤተ ዘመድ ለቅሶ ከመቀመጡ በፊት እናቴንና ቤተሰቦቼን አረጋግ

- Advertisement -
Sidebar AD

” እናቴ ‘ ልጅሽ ሞቷል ‘ ተብላ እያለቀሰች ነበር ፤ ነገር ግን ቤተ ዘመድ ለቅሶ ከመቀመጡ በፊት እናቴንና ቤተሰቦቼን አረጋግቻለሁ ” – አብዮት ጩሎ

➡️ ” ‘ ሞቷል ‘ እየተባለ ፎቶዬ በተሰራጨበት ማግስት የ2ኛ ዲግሪ መመረቂያ ፅሑፌን አቅርቤ መመረቄን አረጋግጫለሁ ! ”

#Ethiopia | ትላንት የወላይታ ዲቻ እግር ኳስ ቡድን ከሲዳማ ቡና አቻው ጋር የነበረው የኢትዮጵያ ዋንጫ የፍፃሜ ጨዋታ ያለ ደጋፊ በዝግ ስታዲየም እንዲደረግ ከመወሰኑ ጋር በተያያዘ በተለያዩ ማህበራዊ ሚዲያዎች ” በፀጥታ ሃይሎች ደጋፊዎች (የወላይታ ዲቻ) ተገደሉ ” እየተባለ መረጃዎች ሲሰራጩ ነበር።

ነገር ግን ክለቡ መረጃዎቹ ውሸት መሆናቸውንና ” አንድም ደጋፊ አለመሞቱን ” ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ በዛሬው ዕለት ባደረገዉ ተጨማሪ ማጣራት በርካቶች በማህበራዊ ትስስር ገፆች የተቀባበሉትና ” ሞተ/ተገደለ ” የተባለው ወጣት ጉዳይ ሀሰተኛ መረጃ መሆኑንና ወጣቱ በሕይወት መኖሩን ከራሱ አንደበት አረጋግጧል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ከላይ በፎቶው የሚታየውንና ” ተገደለ / ሞተ ” ተብሎ በስፋት በማህበራዊ ሚዲያ የተወራበትን ወጣት አብዮት ጩሎ አገኝቶ አነጋግሯል።

” የወላይታ ዲቻ ቀንደኛ ደጋፊ ብሆንም በጨዋታው ዕለት ማግስት የ2ኛ ዲግሪ መመረቂያ ፅሑፌን የማቀርበብት ዕለት ስለነበር ወደ አዲስ አበባ አልሄድኩም ” ያለው አብዮት ” ነገር ግን ከጨዋታው መጠናቀቅ በኋላ በበርካታ የማህበራዊ ሚዲያዎች ፎቶዬ እየተሰራጨ ‘በፀጥታ ሃይሎች ተገድሏል’ የሚል መረጃ ደጋግሜ ስመለከት በጣም ነበር የደነገጥኩት ” ብሏል።

በወላይታ ዲቻ የስፖርት ክለብ ማለያ የተነሳውና ብዙ የማህበራዊ ሚዲያዎች ያሰራጩት ፎቶ የራሱ ቢሆንም ፎቶውን ግን የተነሳው ትላንት እንዳልነበር አረጋግጧል።

” አሁን ላይ እኔም ተረጋግቻለሁ ” የሚለዉ ወጣት አብዮት ” በወቅቱ ወደ እናቴ ስደውል ‘ ሞቷል ‘ ተብላ እያለቀሰች ነበር ፤ ነገር ግን ቤተ ዘመድ ለቅሶ ከመቀመጡ በፊት እናቴንና ቤተሰቦቼን አረጋግቻለሁ ” ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግሯል።

” እኔ ‘ ሞቷል ‘ እየተባለ ፎቶዬ በተሰራጨበት ማግስት የ2ኛ ዲግሪ መመረቂያ ፅሑፌን ያቀረብኩበትና መመረቄን ያረጋገጥኩበት ነበር ፤ ፈታኞቼና አማካሪዎቼ በተረጋጋ መንፈስ ጥናታዊ ፅሑፌን እንዳቀርብ አግዘዉኛል ” ሲል አክሏል።
#Tikvah





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: