ኑ እንወቃቀስ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ቀደምት አባቶች እንሰት ለምግብነት የሚውል ተክል መሆኑን አጥንተው አገኙት። እናቶቻችን እንጨት የሚመስል ተክል እንሰት ፍቀው በዚያ ሁሉ ሂደት አልፈው ቆጮ፣ ከቆጮም ቡ’ላ ማውጣት ቻሉበት። ተራቀቁበት። የቀደሙቱ በእንሰት ተክል የምግብ ዋስትናቸውን አረጋግጠው ተንቀባረው ለዘመናት ኖሩበት።

እኛ የዘመንን፣ ዘመናዊ ትምህርት የተማርን፣ የተመራመርን በእነሱ እውቀት ላይ ምን ጨመርን? እናቶቻችን አንድ እግራቸውን ሜታ (መፋቂያ) ላይ ሰቅለው የሚፍቁበትን አፋፋቅ እንኳን በወጉ ማቅለል አልቻልንም።

የግብርና ኮሌጆቻችንና የቴክኒክና ሙያ ኮሌጆቻችን ለተለያዩ ኹነቶች መርሃግብር ማሟያ የሚሆኑ የቴክኖሎጂ ናሙናዎችን ከማቅረብ በዘለለ የማህበረሰቡ ሥራ የሚያቃልሉና ችግር የሚቀርፉ ዘመናዊ ተክኖሎጂዎችን በተጨባጭ ሲያቀርቡ አይስተዋሉም። ሙከራዎቹ ከአንድ ቀን ዜና ወይም የኮንፈራንስ Presentation ፍጆታ ሲያልፉ እምብዛም አይታዩም። የቱ ጋ ይሆን የተቆለፈብን? እስኪ እናውጋ!!
#samuel_belayneh


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2