ኢራን ወደ ውይይት የመግባት ጥብቅ ፍላጎት እንዳላት ተገለጸ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | እስራኤል በኢራን ዋና ከተማ ቴህራን ሰማይ ላይ የአየር የበላይነት እንዳላት እየገለጸች ሲሆን፤ ኢራን ከአሜሪካና ከእስራኤል ጋር የመነጋገርና ግጭቱን የማብረድ ፍላጎት ማሳየቷ ተዘግቧል፡፡

ኢራን በኒዩክለር መርሃ ግብሯ ጉዳይ ከዋይት ሃውስ ጋር የተጀመረውን ውይይት መቀጠል እንዲሁም የተኩስ አቁም በማድረግ ከእስራኤል ጋር የገባችበትን ግጭት የማብረድ ፍላጎት እንዳላት ነው የተነገረው፡፡

ኢራን በእስራኤል ሚሳይሎች እየተደበደበች ቢሆንም፣ የተኩስ ማቆም ለማድረግና ወደ ዲፕሎማሲያዊ እንቅስቃሴ ለመመለስ ጥብቅ ፍላጎት እንዳላት ለአሜሪካ፣ ለእስራኤል እንዲሁም ለአሜሪካ አጋር አረብ መንግሥታት አሳውቃለች ተብሏል፡፡

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ በበኩላቸው፣ ኢራን የመነጋገር ፍላጎት እንዳላት አረጋግጠው፣ ሁለቱ አገራት ስምምነት ላይ እንደሚደርሱ ያላቸውን እምነት መግለጻቸውን ኒውስማክስ ዘግቧል፡፡
#addis_admas





Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: