ዩኒሊቨር በአዲሱ የኢንቨስትመንት ህግ ቀዳሚ የአስመጪነት ፈቀድ የወሰደ የውጭ ኩባንያ ሆነ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | በፍጆታ እቃ ምርት ስሙ በአለም የገነነው የብሪታኒያ–ደች ኩባንያ ኢትዮጵያን ጨምሮ በበርካታ አገራት ውስጥ የምርት ማእከል ያለው መሆኑ ይታወቃል።

መንግስት እያላላ ባለው የኢንቨስትመንት ህግ መሰረት ኩባንያው በአስመጪነት ቢዝነስ ለመሰማራት ፈቃድ እንዲወስድ አስችሎታል።

ቀደም ሲል በነበረው ህግ በአገር ውስጥ አስመጪዎች ብቻ መግባት ይፈቀዱ የነበሩ ምርቶቹን እራሱ ማስገባት እንደሚጀምር የገለፀው ዩኒሊቨር የተለያዩ ቫዝሊን ምርቶቹን በማስገባት በአከፋፋዮቹ በኩል በቅርቡ ለገበያ እንደሚያቀርብም ነው ለፎርቹን ያስታወቀው።

የውጭ ኢንቨስተሮችን እንቅስቃሴ በማስፋት ኩባንየዎች በጅምላ፣ ችርቻሮ አስመጪ እና ላኪ ንግድ ውስጥ እንዲገቡ መንግስት ህጎቹን እያላላ መሆኑ ይታወሳል።

ይህም የአለም ንግድ ድርጅትን ለመቀላቀል የሚረዳ መሆኑ ይታወቃል።

#ቅዳሜገበያ


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1