መቀሌ ዩኒቨርሲቲን ተማምኜ በባዶ ሆዴ እያደርኩኝ ነው ጎዳና ልወጣ ነው የመመረቂያ ሱፍ እንኳን ሳላሰፋ በ ቲሸርት አሳለፍኩ
ይድረስ :- ለመቀለ ዩንቨሲቲ አስተዳደር
የ መቀለ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ በ ኢኮኖሚ ምንም የለኝም ግን የግድ ገንዘብ ያስፈልገኝ ስለነበር ተማሙቼ non cafe ሞልቼ ገንዘቤን እየተጠባበኩኝ ነበር ሆኖም ግን እሱን ተማምኜ ተበድሬ የበላሁት ገንዘብ ኣሁን እንሰጣችሁም ብለው ከለከሉን
እኔብቻ ሳልሆን ብዙ ተማሪዎች አለን እናም በዚ ችግር ምንም አቅም ስሌለኝ አይደለም ብድሬን ልከፍል ቀርቶ የመመረቂያ ሱፍ እንኳን ሳላሰፋ በ ቲሸርት እንዳሳልፈው ተገድጃለሁ
ይህ ሁሉ ሲሆን ግን ዩኒቭርሲቲው ነገ ዛሬ ብሩ ይገባላቹሃል ጠብቁ እያሉን ነበር ሆኖም ግን ኣሁን ላይ ገንዘባችን እንደወሰድን በሲስተም ላይ አስፍረው በጀት የለንም ብለው ዘጉን አሁን ማንን አቤት እንበል እጄ ላይ ምንም የለኝም የቤት ኪራይ እንዳልከራይ የነበረብኝን ብድር ከፍየ ኣሁን በባዶ ሆዴ እያደርኩኝ ነው በቅርቡ ጎዳና መውጣቴ አይቀርም
ምን ብንል ማንም አይሰማንም በጭንቀት ብዙ መጥፎ ውሳኔ እያሰብኩኝ ነው ቢያንስ እንኳን ያቺን ገንዘብ ቢለቁልኝ ሊስትሮ ጀምሬ አልያም ዶሮ እርባታ ለመክፈት አስቤ ነበር መመረቄ ትርጉም አጣሁበት ራሴን ላጠ& ቀን እየቆጠርኩኝ ነው መፍትሔ ካላችሁ በማርያም
Source: Yeneta Tube









No comments yet.