‹‹ዳኙ ሊመታ ነው፤ ዳኙ ገላግለን . . . ወይኔ ዳኙ አ – ገ – ባ -፤ ደንሶ አገባ ዳኙ፣ ቀኝ አሳይቶ ግራ፣ ግራ አሳይቶ ቀኝ በጣም አስደናቂ ግብ ነው . . . ›› ትንፋሹ ቁርጥ ቁርጥ እያለ ደስታና ሲቃ፣ ስሜትም በተቀላቀለበት ድምፀት ታኅሣሥ 17 ቀን 1980 ዓ.ም. ያስተጋባው ታዋቂው የስፖርት ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ነበረ፡፡
በአገራችን ኢትዮጵያ በስፓርት ጋዜጠኝነት ከቀደምቶቹ አቶ ፍቅሩ ኪዳኔ፣ የጅብራተሩ አለት ይድነቃቸው ተሰማ፣ ይንበርበሩ ምትኬ፣ ጎርፍነህ ይመርና አይተኬው የቀጥታ ዘገባ ባለሟሉ የድሬዳዋ ፍሬ ደምሴ ዳምጤ በቀዳሚነት ይጠቀሳሉ። ጋዜጠና ደምሴ ዳምጤን በሬዲዮ መስማት ሜዳው ውስጥ ቀጥታ ጫወታን ከመከታተል የበለጠ ሃሴትን ያጎናጽፋል። በዚህም በዘመኑ ”እግር ካስን በሬዲዮ የሚያሳይ!” ተብሎለታል።
ስፖርት ዘጋቢነት ድንቅ የሆኑ ባለሙያዎች ስራቸውን አስቀምጠውልን አልፈዋል። በርካቶች ደግሞ የነሱን ፈለግ ተከትለው ድርሻቸውን ተወጥተዋል። ገና በለጋ እድሜው በ16 ዓመቱ ወደ ስፓርት ጋዜጠኝነት ሙያ የተሰማራው ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤም ከነዚህ ተርታ ይመደባል። ይህን የአገር ቅርስ ለአፍታ እናስታውሰው።
በኢትዮጵያ ስፖርት ጋዜጠኝነት ታሪክ ሁነኛ ሥፍራ ያለው ደምሴ፣ የስፖርት ዜናዊነቱን የጀመረው ምሥራቃዊቷ ድሬዳዋ ከተማ በአማተርነት እየዘገበ ወደ አዲስ አበባ መላክ በጀመረበት ጊዜ ነው፡፡ በተለይ በኢትዮጵያና ብሥራተ ወንጌል ሬዲዮ ጣቢያዎች፣ በኢትዮጵያ ቴሌቪዥንም ጋዜጠኛና ‹‹የስፖርት ፋና›› ጋዜጣ መሥራች ከነበረው ታላቁ ጋዜጠኛ ሰሎሞን ተሰማ ጋር ቅርበት ስለነበረው ከድሬዳዋ የሐረርጌን ስፖርታዊ እንቅስቃሴ እየዘገበ ይልክ ነበር፡፡
ጋዜጠኛ ደምሴ ተወልዶ ያደገው ድሬደዋ ሲሆን በኢትዮጵያ ሬድዮ ከመቀጠሩ በፊት የስፖርት ፊሪላንስ ጋዜጠኛ ሆኖ ከትውልድ ስፍራው ይሰራ ነበር፡፡
ጋዜጠኛ ደምሴ ለኢትዮጵያ ስፖርት እድገት ደከመኝ ሳይል የሰራና በዚህም በህዝብ ዘንድ ከፍተኛ ተወዳጅነትን ያተረፈ ባለሙያ ነበር፡፡
በሙያውም አትላንታ፣አቴንስና ቤጅንግ ኦሎምፒኮችን በስፍራው በመገኘት ለኢትዮጵያ ህዝብ አስተላልፏል፡፡
ጋዜጠኛ ደምሴ ዳምጤ ለ 40 አመት ከሁለት ወር ያህል የ ኢትዮጵያ እግር ኳስናአትሌቲክስ ነባራዊ ምስክር ነው ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምሥራቅና በመካ ከለኛው አፍሪካ ዋንጫ ድል ሲያደርግ ጋዜጠኛ ደምሴ በውስጣዊና ውጫዊ ደስታረስርሷል ፡ በአትሌቲክሱም ዘርፍ በጀግኖች አትሌቶች ድል የኢትዮጵያ ባንዲራ ከፍብሎ ሲውለበለብ የደስታ ሳግ እየተናነቀው ድሉን በልዩ የስሜት የበላይነት ዘግቧል፡፡ ከ ሞስኮ እስከ ባርሴሎና ፡ከ አትላንታ እስከ ሲድኒ ፡ ከ አቴንስ እስከ ቤጂንግ ደምሴየ ሀገር ኩራቶች አብሪ ከዋክብቶች የደመቁበትን ደማቅድል ለሚወደው ህዝብበአይረሴና ተናፋቂ ድምፁ አስተጋብቷል ፡ ታሪክ ሲሰራ ከታሪክ ቀማሪዎች ጋርተገኝቷል፡፡ ታሪካቸውን ሰንዷል እነሆ አብሮም ታሪክ ሆኗል ፡፡፡
ጋዜጠኛ ደምሴ በ 40 ዓመታት የኢትዮጵያ ስፖርት ውጣ ውረድ ውስጥ ደሙእስኪንተከተክ ድረስ ተችቷል፡፡ ጮኋል ገምግሟል ፡፡ ስፖርትና ስፖርትን ብቻ ዘግቧል፡፡ ስነ- ስፖርትን ዘምሯል፡፡ ለብዙ ወጣቶች በተለያዩ ስፖርቶች መሳተፍና የስፖርት ጋዜጠኞች መፈጠር ከፍላጎት መቀስቀሻ ምንጭነት ያለፈ የሙያ ስነ ምሳሌ ሆኗል ፡፡
ጋዜጠኛ ደምሴ የሀገር ፍቅር ያለው ባለሙያ ነው ፡፡ የሀገር ፍቅሩንም በስራው ላይ ባሳየው ትጋት አስመስክሯል፡፡ ለሙያውም ዋጋ ከፍሏል ፡፡ ለምሳሌ ደራርቱ ቱሉበባርሴሎና ኦሎምፒክ ያሸነፈች ጊዜ ሌሊት በእግሩ ከቤቱ እስከ ሬዲዮ ጣቢያ ድረስ መሄዱ ትልቅ ምስክር ነው ፡፡ ጥርሱን በስፖርት ዘገባ ነቅሏል ለማለት ይቻላል ፡፡ ለአንድባለሙያ በህዝብ ዘንድ መወደድ ከባድ ነው፡፡ ደምሴ ግን ፍቅሩን አግኝቶታል ፡፡ብንል ማጋነን አይሆንም ።


Source: Yeneta Tube









No comments yet.