#Ethiopia | የኢትዮ ጂቡቲ ባቡር ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ የኢትዮ-ጂቡቲ የባቡር መስመር የባቡር መሀንዲሶች (Rolling Stock) ያስመዘገቧቸውን ስኬቶች አስመልክተው በማህበራዊ የትስስር ገፃቸው ባስተላለፉት መልዕክት “ህልሞችን ወደ እውነት እየለወጥን እንገኛለን” ብለዋል።
ሮሊንግ ስቶክ የስራ ክፍል ውሰጥ ፈተናዎችን እያለፉ የላቀ ስኬት እያስመዘገቡ የሚገኙ የባቡር መሀንዲሶችን በማየቴ ያለኝ እምነትና ተስፋን ከፍ አድርገውታል ብለዋል።
በክፍሉ የሚገኙ መሀንዲሶች የባቡር መስመሮችን ትርጉም ባለው መልኩ ማስተዳደር መቻላቸው፣ የማይደፈሩ የሚመስሉ ውስብስብ ተግዳሮቶችን በብቃት ማለፋቸው የሚደነቅ ነው ብለዋል።
በራስ አቅም ችግሮችን ለይቶ መፍትሔ መስጠት ብቻ ሳይሆን የአገር ውስጥ እውቀትን ወደ እውነታ እየለወጡ ብሔራዊ ብልጽግናን በማቀጣጠል እና የኢትዮጵያ የወደፊት ዕጣ ፈንታ በፈጣን መንገድ ላይ መሆኑን እያረጋገጡ የሚገኙ በመሆኑ ልዩ ቦታ ይሰጠዋል።
በዚህ አይነት ቁርጠኝነት ከቀጠልን ኢትዮጵያን እና የአፍሪካ ቀንድን ከመቼውም ጊዜ በላይ በባቡር መሠረተ ልማት የማስተሳሰር ጥረታችን እውን ይሆናል።
ገና ይቀረናል፣ ምርጡ ገና ይመጣል!
ሲሉ ዋና ስራ አስፈፃሚ ታከለ ኡማ መልዕክታቸውን አጠናቀዋል።



Source: GetuTemesgen









No comments yet.