ሴቶች “ገላግሌ” እያሉ የሚገልፁት ሹሩባ

- Advertisement -
Sidebar AD

#Ethiopia | ሹሩባ በተለይ በክረምት ወቅት ሴቶች ራሳቸውን ለማስዋብ እና የፀጉራቸውን ደህንነት ለመጠበቅ የሚመርጡት ነው።

በክረምት ካለው አየር ጋር የሚሄድ፣ በዝናብ እና በቅዝቃዜ የማይበላሽ በመሆኑ በብዙዎች ዘንድ ተመራጭ ነው።

ሹሩባ በየቀኑ ማስተካከል እና ቅርፅ ማስያዝ የማይሻ በመሆኑ በተለይ የተጣበበ ጊዜ ያላቸው እንስቶች “ገላግሌ” ሲሉ ይገልፁታል።

ይህን የብዙዎች ፍላጎት የተገነዘቡ የከተማዋ ቤተ-ውበቶች ሹሩባን በዓይነት በዓይነቱ እያደረጉ እንደሚሾርቡ የፀጉር ባለሙያው ኤርሚያስ ይናገራል።

ወቅቱን ተከትሎ በርከት ያሉ ደንበኞቹ ፀጉራቸውን በእሳት መሳሪያ ከመስተካከል (ከመተኮስ) ይልቅ ሹሩባ መሠራትን መምረጣቸውን ባለሙያው ለኢቲቪ ገልጿል።

ሹሩባ በፀጉር ብቻ ሲሰራ 200 ብር እንደሚያስከፍል የገለፀው ባለሙያው፤ በዊግ ሲሆን እንደ ብዛቱ እና ዓይነቱ ክፍያው እንደሚለያይ ተናግሯል።

እንደዛሬ በእሳት አማካኝነት ፀጉርን ማስተካከል ሳይጀመር ሹሩባ ወቅትን ጠብቆ ሳይሆን የሁልጊዜ የፀጉር ፋሽን እንደነበር ያልደበዘዘ ትውስታ ነው።

ሆኖም አሁን ላይ የክረምቱን አየር ምክንያት አድርጎ እንደ ፋሽን የሚዘወተረው ሹሩባ በተለያየ አሠራር እና ዲዛይን ከፍ ማለቱን ባለሙያዎች ይገልፃሉ።

በአፎሚያ ክበበው




Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2