ውሾች በአዲስ አበባ የውበት ሳሎን አገልግሎት ማግኘት ጀመሩ!በኢትዮጵያ ውስጥም እንደ አለም የውሻ እንክብካቤ እየተሻሻለ ነው። …

- Advertisement -
Sidebar AD
ውሾች በአዲስ አበባ የውበት ሳሎን
አገልግሎት ማግኘት ጀመሩ!
በኢትዮጵያ ውስጥም እንደ አለም የውሻ እንክብካቤ እየተሻሻለ ነው። በአዲስ አበባ፣ በተለይም አሁን ሞሞፔት የሚባል የውሾች የውበት ሳሎን ተከፍቷል።
ብዙ ሰዎች ዘንድ የቅንጦት ቢመስልም የውሾችን ጤና እና ንጽህና ለመጠበቅ ግን አስፈላጊ አገልግሎት እየሰጠ ነው።
ይህ ሳሎን ውሾች ሙሉ የሰውነት እንክብካቤ የሚያገኙበት ቦታ ነው።
* ከጥፍር እና
* ከፀጉር መስተካከል
* እስከ ጥርስ መቦረሽ ያሉ አገልግሎቶችን ያጠቃልላል።
ሳሎኑ ውስጥ ሞሮኮ ባዝን የመሳሰሉ አገልግሎቶችም ይሰጣሉ።
የሳሎኑ ሰራተኞች እንደሚሉት ለውሾች አገልግሎት ላይ የሚውሉ ቁሳቁሶች በሙሉ ለውሾች ብቻ ተብለው የተዘጋጁ እና ጥራት ያላቸው ናቸው።
ይህ ደግሞ የውሾችን ጤንነት ከግምት ውስጥ ያስገባ እንክብካቤ ነው።
ይህ አዲስ አገልግሎት የውሻ ባለቤቶች ውሾቻቸውን በጥሩ ሁኔታ እንዲያድጉ እና እንዲንከባከቡ እድል ይሰጣል። የእንስሳትን ደህንነት ከፍ ለማድረግም ትልቅ አስተዋፅኦ አለው።
@Seledadotio
@Seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2