ከኬሚካል ነጻ የሆነ የህጻናት ሻምፖ እና ኮንዲሽነር ለገበያ ቀረበ

- Advertisement -
Sidebar AD


‎#FastMereja I ኤልመን ማኑፋክቸሪንግ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማህበር በሃገራችን የመጀመርያ የሆነውን ከሰልፌት፤ ከፓራቢን እና ከሚንራል ኦይል ነፃ የሆነ እና ለህፃናት ታሳቢ በማድረግ የተመረተውን “Doka kids Shampoo” እና “Doka kids Conditioner” ወደ ገበያ ማስገባቱን በዛሬው ዕለት መስከረም 29/2018 ዓ/ም በጎልደን ቱሊፕ ሆቴል በተሰጠው መግለጫ አሳውቀዋል።

የዶቃ የልጆች ሻምፖ እና ኮንዲሽነር ከሰልፌት እና ከምንም አይነት ሚነራል ኦይሎች እንዲሁም ምንም አይነት ፓራቢን ያልተጨመረበት መሆኑ ተነግሯል።

ሻምፑ ልጆች አይን ውስጥ ቢገባም የማይቆጠቁጥ፣ የማያስለቅስ፣ የፀጉርን ተፈጥሯዊ ወዝን እንደጠበቀ ያፀዳል
የፀጉር የርጥበት መጠንን ይጠብቃል ተብሏል።

የአልሞንድ ዘይት፣ Castor ዘይት፣ ቫይታሚን ኢ ንጥረ ነገሮች ይዟል።

#ቢዝነስ






Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: