በኤስ.ፒ.ሲ. (SPC) የወለል ንጣፍ እና ግድግዳ መሸፈኛ ቁሳቁስ ምርቶች ላይ ትኩረቱን ያደረገ ውይይት ተደረገ

- Advertisement -
Sidebar AD

📌ሪሪ አዲስ ምርቱን አስተዋውቋል

#Ethiopia | ሪሪ ፕሮጀክት ዴቨሎፕር ኃላ/የተ/የግ/ ማህበር የሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ አባልና የሚድሮክ የማዕድን ዘርፍ ኩባንያ ሲሆን በኮንስትራክሽን ፣ በፍሎሪንግ ፣በኢንቴሬር ዲዛይን እና የወለል ንጣፎችን በእንጨት፣ በድንጋይና በእምነበረድ ተፈጥሯዊ ዕይታን የጠበቁ በተለያዩ ቀለማት እና ዲዛይኖች ያመርታል፡፡

የኢትዮጵያ የኮንስትራክሽን ዘርፍ በማይቋረጥ እድገት ውስጥ እየተጓዘ ያለ ሲሆን ይህም እንደኛ ባሉ ታዳጊ ሀገራት ጭምር የሚስተዋል የጋራ ጠባይ ነው።

የበዙ የኮንስትራክሽን ስራዎች በአራቱም የሃገሪቱ አቅጣጫዎች በስራ ላይ ቢሆኑም ጥራት ያላቸው ግብአቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ማግኘት በሚታሰበው ልክ ቀላል አይደለም።

ለዚህም በዋናነት የሚጠቀሰው ባለድርሻ አካላት ተቀራርበው አለመስራት እና ችግሮች ላይ ውይይት አለማድረግ ነው።

ሪሪ ፕሮጀክት ዴቨሎፕር ኃላ/የተ/የግ/ ማህበር
ከኤም ቲቲ አርክቴክትስ ኤንድ ኢንጂነሪንግ ኃላ/የተ/የግ/ ማህበር ጋር በመተባበር በኤስ.ፒ.ሲ. (SPC) የወለል ንጣፍ እና ግድግዳ መሸፈኛ ቁሳቁስ ምርቶች ላይ ፓናል ውይይት አካሄዷል።

በውይይቱም ፈጠራና የምርት ጥራትን ማስጠበቅ በሚቻልባቸው ጉዳዮች ላይ የዘርፉ ተዋናዮች አርክቴክቶች፣ መሐንዲሶች፣ አማካሪዎች እና የኢንዱስትሪዉ አጋሮች ሰፊ ዉይይት ያደረጉ ሲሆን በርካታ የመፍትሄ ሃሳቦችን አንስተዋል፡፡

ኤስ.ፒ.ሲ. (SPC) የወለል ንጣፍ እና ግድግዳ መሸፈኛ ቁሳቁስ ምርቶች አዲሱ የውብ የኮንስትራክሽን አጨራረስ መገለጫ እየሆነ የመጣ ሲሆን ስነ ውበቱን ሳይለቅ የረጅም ዓመታት አገልግሎት ያለው በመሆኑ ሁሉም ሊመርጡ እንደሚገባ ተገልጿል።

የምድር የመሸከም አቅም የተወሰነ በመሆኑ እንደ ኤስ.ፒ.ሲ ያሉ ቀላል ግብአቶችን ወደ ሀገራች የኮንስትራክሽን ገበያ በፍጥነት እና በብዛት እንዲገቡ ያስፈልጋል ተብሏል።

ሪሪ ፕሮጀክት ዴቨሎፕር ኃላ/የተ/የግ/ማህበር በ2014 የተመሠረተ ሲሆን አሁን ላይ ውሃ የማያሰርግ ለአገጣጠም ቀላል የማያንሸራትት እሳትን የሚቋቋም የወለል ንጣፍ እና ግድግዳ መሸፈኛ ቁሳቁስ ምርቶችን እያመረተ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን ዩቪ ቦርድ (UV Board) እና ደብልዩ ፒ ሲ (WPC) የተሰኙ አዲስ ምርቶቹን አስተዋውቋል።

ሚድሮክ ኢንቨስትመንት ግሩፕ በ6 የተለያዩ ዘርፎች የተዋቀሩ 45 ድርጅቶችን የያዘና ከ79 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ዜጎች የስራ እድል የፈጠረ ድርጅት ነው፡፡






Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: