እነ ዮሃንስ ዳንኤል ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጠየፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ከኢትዮጵያ አ…

- Advertisement -
Sidebar AD
እነ ዮሃንስ ዳንኤል ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ተሰጠ
የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ደህንነት ጋር ተያይዞ በወንጀል የተከሰሱት እነ ዮሃንስ ዳንኤል (ጆን ዳንኤል) በእስራት እንዲቀጡ ወስኖ የታሰሩት በቂ ስለሆነ ከእስር እንዲፈቱ ትዕዛዝ ሰጠ።
በተጨማሪም ዐቃቤ ሕግ 1ኛ ተከሳሽ ጆን ዳንኤል ላይ በ3ኛ ክስ የኮምፒዩተር ወንጀል ለመቆጣጠር የወጣውን አዋጅ ቁጥር 958/2008 አንቀጽ 13 ንዑስ ቁጥር 3 ሥር የተመለከተውን ድንጋጌ በመተላለፍ ክስተቱን ቲክቶክ በተባለ ማህበራዊ ሚዲያ በተንቀሳቃሽ ምስል ቀርጾ በቀጥታ ስርጭት ማስተላለፍ የሚል ክስ አቅርቦበት ነበር።
ተከሳሾቹ በተከሰሱበት የህግ አንቀፅ ጥፋተኛ የተባሉ ሲሆን ችሎቱ በዛሬው ዕለት የዐቃቤ ሕግን የቅጣት ማክበጃ እና የተከሳሾችን የቅጣት ማቅለያ መርምሮ ውሳኔ አሳልፏል።
በዚህም ተከሶሾቹ የተከሱበት የህግ አንቀፅ ቀላል እስራትን የሚያስከትል በመሆኑ 1ኛ ተከሳሽ በአንድ አመት ከአራት ወር፤ 2ኛ፣ 3ኛ እና 6ኛ ተከሳሾች በስምንት ወር እንዲሁም 4ኛ ተከሳሽ በ10 ወር እስራት እንዲቀጡ ወስኗል።
በመሆኑም ተከሳሾቹ በእስር ላይ የቆዩበት ጊዜ ተሰልቶ ተከሳሾቹ እንዲፈቱ የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት 1ኛ ልዩ ልዩ ከባድ ወንጀል ችሎት ውሳኔ አሳልፏል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1