የኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ በሀገሪቱ ውስጥ ሲሰሩ የነበሩ የ22 የስፖርት ውድድር ውርርድ ድርጅቶች ፈቃድ ከ ህዳር 25 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ታግዷል።
ይህ ውሳኔ በዘርፉ ላይ ከፍተኛ ለውጥ የሚያመጣ ሲሆን፣ ውርርድ ተጫዋቾችና ባለድርሻ አካላት ትኩረት እንዲሰጡት ጥሪ ቀርቧል።
በኢትዮጵያ ሎተሪ አገልግሎት አማካኝነት ፈቃዳቸው የታገደባቸውን ዋና ዋና የስፖርት ውርርድ ድርጅቶች እነሆ፡
1. ዳሽ ቤት ባለ አንድ አባል ኃ/የተ/የግ/ማህበር
2. ዋልያ ስፖርት ኃ/የ/የግ/ማህበር
3. ኤክስኔት ሶሎሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ቱ ኤክስ ቤት)
4. ኤች ዲ ኤም /አፍሮ/ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
5. ብላክ ፐርል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
6. አይከኒክ ስፖርት ኢንተርቴይመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
7. ጃምቦ ቤት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
8. ዳአባአክ ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
9. ኢቲኤል (ኪዉክ) ኃ/የ/የግ/ማህበር
10. ቤት አራዳ ስፖርት እና ኢንተርቴመንት ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ሱፐር)
11. ቫሞስ ኢንተርቴይመንት ኃ/የ/የግ/ማህበር
12. ፍላሽ ስፖርት ውርርድ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
13. ሁለገብ ኦንላይን ሶሎሽን ኃ/የ/የግ/ማህበር
14. ዘመን ስፖርት ቤቲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
15. ሁሉ ጌሚንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
16. አዲስ ቴልኮ ሰርቢስ አክሲዮን ማህበር (ቤቲካ ስፖርት ውርረድ)
17. ዩኒክ /መላ/ ስፖርት ቤቲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር
18. ቶቶ ስፖርት ሶልሽን ኃ/የተ/የግ/ማህበር
19. ኩኩሉ ስፖርት ስፖርት ኃ/የተ/የግ/ማህበር
20. መርኬ ቤቲንግ ኃ/የተ/የግ/ማህበር (ሻምፒዮን)
21. ቤት ዘጠኝ ዘጠና አራት ኃላ/የተ/የግ/ማህበር
22. ሀሪፍ የስፖርት አገ/ኃ/የተ/የግ/ማህበር
ማስታወሻ: የፈቃድ መታገድ ምክንያቶች ዝርዝር ባይገለጽም፣ ድርጊቱ መንግስት በዘርፉ ላይ ያለውን ቁጥጥር ማጥበቁን ያመለክታል።
Via ብሔራዊ ሎተሪ (National Lottery)
Source: Yeneta Tube









No comments yet.