አቶ ጌታቸው ረዳ የፕሪቶርያው የሠላም ሥምምነት እንደ ግዴታ ሊወሰድ ይገባል አሉ።
የቀድሞው የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንትና የአሁኑ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምሥራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ፣ የፕሪቶሪያው የግጭት ማቆም ስምምነቱ ሙሉ ለሙሉ ተግባራዊ የሚሆነው ሁለቱም ወገኖች ከሽኩቻ ወጥተው እንደ ግዴታ ሲወሥዱት ነው ብለዋል፡፡
ጌታቸው፣ ከስምምነቱ መፈረም በኋላ በትግራይ ፖለቲከኞች መካከል የተፈጠረው ችግር ስምምነቱ መኖር አለበት ወይስ የለበትም የሚል ሳይሆን፣ የትግራይን ሽግግርን ማን ይምራ የሚል እንደሆነ ጠቅሠዋል።
አክለውም ፕሪቶሪያ የፖለቲካ ኃይሎች አንድን ስምምነት “ለቡድናዊ ጥቅም” ሲያውሉት ሰላም ምን ያህል እንደሚሸረሸር በግልጽ አሳይቷልም ብለዋል።
የምዕራብ ትግራይ፣ ራያ እና የፌደራሉ ሠራዊት አወጣጥ ጉዳይ በፕሪቶሪያው ድርድር ያልተካተቱት፣ በእነዚህ ጉዳዮች ሳቢያ ድርድሩ ከከሸፈ በትግራይ ሕልውና ላይ የከፋ መዘዝ ይመጣል በሚል ስሌት መሆኑንም አውስተዋል።
የፌደራል መንግሥቱ ተደራዳሪ ልዑክ ወደፊት በትግራይ የሚቋቋመው ጊዜያዊ አስተዳደር በምዕራብ ትግራይ እና ራያ ላይ “ቁጥጥር” እንዳይኖረው የሚከለክል አንቀጽ ለማስገባት ሞክሮ እንደነበር አቶ ጌታቸው የጠቀሱ ሲሆን፣ ሆኖም ያ አንቀጽ ቢገባ ድርድሩ ይከሽፍ ነበር ብለዋል።
@seledadotio

Related Posts
- Advertisement -

No comments yet.