🇪🇹
📌ታዋቂው የማህበራዊ ገጾች ኮከብ አይሾው ስፒድ (IshowSpeed) ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ እንደሆነ ተገለጸ
🔴 በ’የደራው መጽሔት
#Ethiopi | በዓለም አቀፍ ደረጃ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ተከታዮች ያሉትና በከፍተኛ ጉልበት በሚያቀርባቸው የቀጥታ ስርጭት (Livestream) ቪዲዮዎቹ የሚታወቀው አሜሪካዊው የዩቲዩብ ኮከብ ዳረን ዋትኪንስ ጁኒየር (IshowSpeed) ወደ ኢትዮጵያ ሊመጣ መሆኑን ፍንጭ ሰጥቷል።
ተጫዋቹ በቅርቡ በተለያዩ የዓለም ሀገራት እያደረገ የሚገኘውን የጉብኝት አካል አድርጎ ወደ አፍሪካ ቀንድ እንደሚያቀና ተነግሯል።
ስፒድ በተለይም በተለያዩ ሀገራት በሚያደርጋቸው ቆይታዎች የሀገሪቱን ባህል፣ ምግብና ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎች በቀጥታ ስርጭት ለዓለም በማስተዋወቅ ይታወቃል።
ስፒድ ወደ አዲስ አበባ በሚመጣበት ወቅት በከተማዋ የተለያዩ ስፍራዎች በመዘዋወር ከደጋፊዎቹ ጋር እንደሚገናኝና ይህም በሚሊዮኖች ለሚቆጠሩ ተመልካቾቹ በቀጥታ እንደሚተላለፍ ይጠበቃል።
ይህ ዜና በማህበራዊ ሚዲያ ከተሰራጨ ዕለት ጀምሮ በርካታ ኢትዮጵያውያን ወጣቶችና የዩቲዩብ ተከታዮች ከፍተኛ ደስታቸውን እየገለጹ ይገኛሉ።
በቆይታው የአዲስ አበባን ውበት ፣ የኢትዮጵያን ቡና፣ ባህላዊ ምግቦችና ታዋቂ የቱሪስት መስህቦችን ለዓለም አቀፍ ማህበረሰብ ሊያስተዋውቅ እንደሚችል ይገመታል።
አይሾው ስፒድ በቅርቡ በኖርዌይ፣ ጣሊያንና አልባኒያ ባደረጋቸው ጉብኝቶች እጅግ ከፍተኛ ቁጥር ያለው ህዝብ አቀባበል አድርጎለት እንደነበር ይታወሳል። የኢትዮጵያው ጉብኝትም በተመሳሳይ መልኩ ደጋፊዎቹን ወደ አደባባይ እንደሚያወጣ ተገምቷል።
የደራው መጽሔት
”ፀሐይ አትጠልቅም”
Source: GetuTemesgen









No comments yet.