“የመድረክ ሰዓቴ ተሰርቋል” ጆኒ ራጋ በልጅ ሚካኤል (ፋፍ) ላይ ቅሬታውን ገለጸ

- Advertisement -
Sidebar AD

#FastMereja I ባለፈው ቅዳሜ ጥር 23 ቀን 2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል በተካሄደው የሙዚቃ ኮንሰርት ላይ፣ የድምጻዊ ጆኒ ራጋ መድረክ ላይ መቆየት አድናቂዎቹን ሳያረካ ቀርቷል። ለተፈጠረው የሰዓት መጥበብ እና የዝግጅቱ መስተጓጎል ድምጻዊው በታዲያስ አዲስ በኩል ማብራሪያ ሰጥቷል።

​ጆኒ ራጋ እንደገለጸው፣ ለኮንሰርቱ ለ18 ቀናት ያህል ከባንዱ ጋር ከፍተኛ ዝግጅት አድርጎ ነበር። ሆኖም ግን ከእሱ በፊት መድረክ ላይ የወጣው ድምጻዊ ልጅ ሚካኤል (ፋፍ) ከተሰጠው የሰዓት ገደብ በላይ በመቆየቱ የፕሮግራሙን ቅደም ተከተል አዛብቶታል ብሏል።

​”እያንዳንዱ አርቲስት አራት ወይም አምስት ሙዚቃዎችን እንዲያቀርብ ታቅዶ ነበር። ነገር ግን ልጅ ሚካኤል ሰዓቱን አክብሮ ባለመውጣቱ የእኔን የመድረክ ሰዓት ተሻምቶብኛል” ሲል ጆኒ ቅሬታውን ገልጿል።

​በዕለቱ በአዲስ አበባ በርካታ ዝግጅቶች ተሰርዘው የነበረ ቢሆንም፣ የኤግዚቢሽኑ ኮንሰርት ግን በልዩ ሁኔታ እስከ ምሽቱ 5፡00 ሰዓት እንዲቆይ ተፈቅዶለት ነበር። ሆኖም ግን የሰዓት አጠቃቀም ችግሩ መስተካከል ባለመቻሉ፣ የጸጥታ አካላት ዝግጅቱ እንዲያበቃ ጫና ማሳደር ጀመሩ።

​የታቀደው ዝግጅት ከ9 እስከ 10 የሚደርሱ ሙዚቃዎች ቢሆንም የተፈጠረው ተጽዕኖ አዘጋጆቹ ጆኒ ራጋ ሁለት ሙዚቃዎችን ብቻ እንዲጫወት ጠይቀውታል። ጆኒ አድናቂዎቹን ላለማስቀየም “በጉልበት” አራት ሙዚቃዎችን ተጫውቶ ለመውረድ ተገዷል።

​አርቲስቱ መድረክ ላይ አለመግባባት እንዳይፈጠር በማሰብ በልጅ ሚካኤል ላይ ጫና አላደረግኩም ያለ ሲሆን፣ በተፈጠረው ክፍተት ግን ማዘኑን አልሸሸገም። ጆኒ ራጋ “የሚጠበቅብኝን ያህል ባለማቅረቤ አድናቂዎቼን ይቅርታ እጠይቃለሁ” ካለ በኋላ፣ በቀጣይ ሰፊ ዝግጅት ተደርጎበት ይህንን ክፍተት የሚደፍን ትልቅ ኮንሰርት እንደሚያቀርብ ቃል ገብቷል።

​#JohnnyRagga #LijMichael #Faf #EthiopianMusic #AddisAbaba #TadiasAddis #ShowbizEthiopia #ConcertUpdate #ወቅታዊ #ጆኒራጋ #ልጅሚካኤል


Source: FastMereja

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: