—————————————-
📅 የካቲት 12 ቀን 2018 ዓ.ም
📍 ሾውቢዝ
ታዋቂው ድምጻዊ ሳሚ ዳን በክለቡ አርሰናል ወቅታዊ አቋም ላይ ያለውን ስጋትና ጥያቄ በግል የማህበራዊ ሚዲያ ገጹ ላይ ለደጋፊዎች አጋርቷል።
አርሰናል አሁን ባለው ሁኔታ የደረጃ ሰንጠረዡ አራተኛ ውስጥ (Top 4) ለመግባት እራሱ ሊያሰጋት እንደሚችል ስጋቱን ገልጿል።
”በመሀይም የኳስ እውቀቴ ስገመግማት አርሴ ማትችለውን መከላከል ለምን እንደምትመርጥ ግር ይለኛል” ሲል የአሰልጣኙን ስልት ተችቷል።
“አሁን ተስፋችን ፈጣሪ አይደለምን?” በማለትም ነገሮች ከአቅም በላይ እየሆኑ መምጣታቸውን አስፍሯል።
ሳሚ ዳን ለደጋፊዎቹም “ምታውቁ እስኪ እውቀት ልቀቁብኝ” በማለት ክለቡ ለምን ወደ መከላከል እንደሚያመዝን ሙያዊ ማብራሪያ እንዲሰጡት ጋብዟል።
#FastMereja | #Showbiz | #SamiDan | #Arsenal
Source: FastMereja









No comments yet.