በመጋቢት ወር የሚተገበረው አዲሱ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ይፋ ሆነ

- Advertisement -
Sidebar AD



የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ከዛሬ መጋቢት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 8፡00 ጀምሮ ተግባራዊ የሚሆን የአዲስ አበባ ከተማ የነዳጅ ምርቶች የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ ማሻሻያ ማድረጉን አስታወቀ።

​ሚኒስቴሩ ባወጣው መግለጫ መሠረት፣ የዓለም የነዳጅ ዋጋን መነሻ በማድረግ የተወሰነው ይሄው አዲስ መመሪያ፤ በሁሉም የነዳጅ ምርቶች ላይ ተግባራዊ የሚሆን የዋጋ ዝርዝርን አካቷል።

በዚህም መሠረት በዋና ዋና የነዳጅ ምርቶች ላይ የተቀመጠው የችርቻሮ መሸጫ ዋጋ የሚከተለውን ይመስላል፦

👉ቤንዚን፦ በሊትር 132.18 ብር

👉 ነጭ ናፍጣ፦ በሊትር 139.84 ብር

👉 ኬሮሲን፦ በሊትር 146.14 ብር

👉 ቀላል ጥቁር ናፍጣ፦ በሊትር 137.03 ብር

👉 ከባድ ጥቁር ናፍጣ፦ በሊትር 133.45 ብር

👉 የአውሮፕላን ነዳጅ፦ በሊትር 145.23 ብር

​መንግስት ይሄንን የዋጋ ማስተካከያ ተግባራዊ እንዲደረግ የወሰነ ሲሆን፣ የሚመለከታቸው አስፈጻሚ አካላትም ቁጥጥርና ክትትል እንዲያደርጉ መመሪያ መተላለፉ ታውቋል። ይህ አዲስ የዋጋ ዝርዝር ለሕዝብ ይፋ እንዲሆንና በከተማዋ በሚገኙ የነዳጅ ማደያዎች ሁሉ ተግባራዊ እንዲደረግ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።


Source: Yeneta Tube

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom1

You might want to listen to: