ቅንጅቱ በከያኒ ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ላይ የተጣለውን “የጋዜጣዊ መግለጫ ዕገዳ” አወገዘትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተ…

- Advertisement -
Sidebar AD
ቅንጅቱ በከያኒ ቴዎድሮስ ካሳሁን(ቴዲ አፍሮ) ላይ የተጣለውን “የጋዜጣዊ መግለጫ ዕገዳ” አወገዘ
ትብብር ለኢትዮጵያ አንድነት የተሰኘው የአራት የፖለቲካ ፓርቲዎች ቅንጅት፣ ታዋቂው ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን (ቴዲ አፍሮ) አዲስ በሚያወጣው የሙዚቃ ሥራ ዙሪያ ሊሰጠው የነበረው “ጋዜጣዊ መግለጫ መደናቀፉን” በጽኑ እንደሚያወግዝ ገለጸ።
ድርጅቱ ዛሬ ባወጣውና ለአዲስ ማለደዳ በላከላት ይፋዊ መግለጫ እንዳመለከተው፣ ሐሳብን በነጻነት መግለጽ ከማንም የሚሰጥ ችሮታ ሳይሆን የማይገሰስ የሰው ልጆች ተፈጥሯዊ መብት መሆኑን አስታውቋል።
በኢፌዴሪ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 10 ላይ የሰው ልጅ መብቶች የማይገሰሱ መሆናቸው መካተቱን የጠቀሰው ቅንጅቱ፣ ማንኛውም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሐሳቡን የመግለጽ ነጻነት እንዳለው የሚደነግገውን አንቀጽ 29ንም ለአብነት አንስቷል። ይሁን እንጂ በሀገሪቱ ያሉ ሥርዓቶች ራሳቸው ለጻፉት ሕግ ለመገዛት ሲቸገሩና ከሕግ በላይ ሲሆኑ ይታያሉ ሲል ወቅሷል።
ድምጻዊ ቴዎድሮስ ካሳሁን ሊሰጠው የነበረው መግለጫ ስለመታገዱ በይፋዊ ደብዳቤ የተገለጸ ነገር ባይኖርም፣ “የሥርዓቱ ባለሥልጣናት የሚያሳዩት የቃላት ጥቃትና ዘለፋ በእጅ አዙር የተፈጸመ ዕገዳ” መኖሩን እንደሚያመለክት መግለጫው ያስረዳል።
አክሎም፣ አርቲስቱ “ኢትዮጵያዊነትንና ታሪክን መዘከር ነውር በነበረበት ወቅት ወጣቱን በሥነ-ልቦና በመገንባት ላደረገው በጎ አስተዋጽዖ እውቅና ሊሰጠው ሲገባ፣ እንዲህ ያለው መሳደድ አግባብ እንዳልሆነ” ገልጿል።
ትብብሩ ይህን መሰል “ቀጥተኛና ቀጥተኛ ያልኾኑ አፈናዎች ለሌላ ቀውስ በር ከፋችና ገፊ ምክንያቶች ናቸው ብሎ እንደሚወስድ” ገለጿል፡፡
በመሆኑም መንግሥት ክልከላውን በጓዳ ከመፈጸም ይልቅ አርቲስቱ የተደናቀፈበትን መግለጫ እንዲሰጥ ሁኔታዎችን እንዲያመቻች ወይም ከአደናቃፊነት ራሱን እንዲያቅብ ጥሪ አቅርቧል። በተጨማሪም የዜጎች የመናገር ነጻነት እንዲከበርና ፍትሕ በግለሰቦችና በካድሬዎች እጅ እንዳይወድቅ በጥብቅ አሳስቧል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: