በህንድ የካሽሚር ግዛት ለኢራን 2 ሚሊዮን ዶላር አሰባሰቡበኢራን ውስጥ የርዕዮተ-ዓለም ተጽዕኖ እየደበዘዘ ቢመጣም፤ በህንድ በሚ…

- Advertisement -
Sidebar AD
በህንድ የካሽሚር ግዛት ለኢራን 2 ሚሊዮን ዶላር አሰባሰቡ
በኢራን ውስጥ የርዕዮተ-ዓለም ተጽዕኖ እየደበዘዘ ቢመጣም፤ በህንድ በሚተዳደረው የካሽሚር ግዛት ግን ነገሩ በተቃራኒው ሆኗል።
የኢራኑ የበላይ መሪ አሊ ካሜኒ መገደልን ተከትሎ በካሽሚር የሚገኙ የሺዓ ማህበረሰብ አባላት ለኢራን ድጋፍ የሚውል ወደ 2 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋ ገንዘብ በአጭር ጊዜ ውስጥ በማሰባሰብ ለዓለም አስገራሚ የሆነ የርዕዮተ-ዓለም ቁርኝታቸውን አሳይተዋል።
ይህ የካሽሚር አካባቢ ከኢራን ጋር ባለው ጥልቅ ሃይማኖታዊና ባህላዊ ትስስር ምክንያት “ኢራኒ ሳጊር” (ትንሿ ኢራን) የሚል ቅፅል ስም ተሰጥቶታል።
በየመንደሩ በተዘጋጁ የገንዘብ ማሰባሰቢያ መድረኮች ላይ የኻሜኒ ምስሎች ጎልተው የታዩ ሲሆን፤ ነዋሪዎች ያላቸውን ጥሬ ገንዘብ፣ የወርቅ ጌጣጌጦችንና አልፎ ተርፎም የቤት ውስጥ የመዳብ ቁሳቁሶችን ጭምር በመስጠት ለኢራን ያላቸውን ታማኝነት አረጋግጠዋል።
@seledadotio
@seledadotio

Source: SeledaPost

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2

You might want to listen to: