የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከኢራኑ አቻቸው አባስ አራቅቺ ጋር ተነጋገሩ፡፡
ሁለቱ ሚንስትሮች በስልክ ባደረጉት ውይይት ዋንግ የሆርሙዝ ወሽመጥን ለመክፈት ዓለም አቀፍ ፍላጎት እንዳለ ገልፀዋል።
የቻይናው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዋንግ ዪ ከኢራኑ አቻቸው አባስ አራቅቺ ጋር ባደረጉት ውይይት በሆርሙዝ የባህር ወሽመጥ ላይ መደበኛ የትራንስፖርት እንቅስቃሴ እንዲቀጥል መጠየቃቸውን ተሰምቷል።
ዋንግ ዪ የኢራን ሉዓላዊነትና ደህንነት ሊከበር የሚገባ ቢሆንም ፣ በወሽመጡ በኩል የሚደረገው የንግድ መርከቦች እንቅስቃሴና ደህንነትም ሊረጋገጥ እንደሚገባ አሳስበዋል።
ወሽመጡ ክፍት ሆኖ እንዲቆይ ሁሉም ወገኖች ከፍተኛ ፍላጎት እንዳላቸው ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ቻይና የተኩስ አቁም ስምምነቱ እንዲቀጥልና ድርድሮች እንዲጀመሩ ድጋፏን እንደምትሰጥም ዋንግ ዪ ጨምረው አሳውቀዋል ያለው ቢቢሲ ነው።
Source: Yeneta Tube









No comments yet.