የቀድሞው የአርሰናል ግብ ጠባቂ አሌክስ

- Advertisement -
Sidebar AD

ማኒንገር በድንገተኛ አደጋ ህይወቱ አለፈ

#Ethiopia | በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ እና በጣሊያን ሴሪ አ ስኬታማ የጨዋታ ዘመናትን ያሳለፈው ኦስትሪያዊው ግብ ጠባቂ አሌክስ ማኒንገር በተከሰተ ድንገተኛ አደጋ ሕይወቱ ማለፉን የሚጠቁሙ ዘገባዎች እየወጡ ይገኛሉ።

ማኒንገር በተከሰተ ድንገተኛ አደጋ ሕይወቱ ማለፉን የሚጠቁሙ ዘገባዎች እየወጡ ይገኛሉ።

የ48 ዓመቱ የቀድሞ ኮከብ ሕይወቱ ሊያልፍ የቻለው የባቡር መስመር በማቋረጥ ላይ እያለ በመኪና አደጋ እንደሆነ ተመልክቷል።

ማኒንገር እ.ኤ.አ በ2017 ከእግር ኳስ ዓለም በይፋ ከተገለለ በኋላ በትውልድ ሀገሩ ኦስትሪያ በንግድ ሥራ ላይ ተሰማርቶ ይገኝ ነበር።

አሌክስ ማኒንገር በተጫዋችነት ዘመኑ በበርካታ ታላላቅ የአውሮፓ ክለቦች ውስጥ ማለፍ የቻለ ድንቅ ግብ ጠባቂ ነበር፦

ከመድፈኞቹ ጋር የፕሪሚየር ሊግ እና የኤፍ ኤ ካፕ (Double) ዋንጫዎችን በማንሳት ደምቆ ታይቷል።ከጣሊያኑ ግዙፍ ክለብ ጋር የሴሪ አ ዋንጫን ማሳካት ችሏል።

በሊቨርፑል፣ ፊዮረንቲና፣ ቦሎኛ እና ቶሪኖ በመሳሰሉ ክለቦች ውስጥም ግልጋሎት ሰጥቷል።

Getu Temesgen – (ጌጡ ተመስገን)
#getutemesgen #getu #fmc
#AlexManninger #Arsenal #Juventus #FootballNews #RestInPeace #Ethiopia #FootballUpdates


Source: GetuTemesgen

Comments

No comments yet.

- Advertisement -
Advertisement post bottom2