🙏
ነቢየ እግዚአብሔር ቅዱስ ኢሳይያስ በትንቢቱ ምእራፍ 7÷14 “እግዚአብሔር ምልክት ይሰጠናል ድንግል በድንግልና ጸንሳ በድንግልና ትወልዳለች ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች፡፡ ትርጓሜውም እግዚአብሔር ከእኛ ጋር ሆነ ማለት ነው፡፡ እርሱም ድንቅ መካር ኃያል የእግዚአብሔር ልጅ ይባላል አለቅነትም በጫንቃው ላይ ይሆናል።” አለን፡፡ በመሆኑም እመቤታችን የአምላክ እናት የእግዚአብሔር እናት ትባላለች። በ325 ዓ.ም በጉባኤ ኒቂያ በነበረው የሲኖዶስ ውይይት ላይ በአደባባይ ተከራክረው ከሐዲያንን ካሳፈሩ 318 ሊቃውንት አንዱ የቆጵሮሱ ሊቀ ጳጳስ ቅዱስ ኤጲፋንዮስ የጌታችንን መለኮታዊ ባህርይ ለሚጠራጠሩ አርዮሳውያንና በተዋሕዶ ሰው ሆኖ መክበሩን ለሚክዱ የተዋሕዶን ምሥጢርና ቅድስት ድንግል ማርያም የመለኮት እናት ስለመሆኗ ሲያስተምር “ኢየሱስ ክርስቶስ ሰውና አምላክ በተዋሕዶ የከበረ ነው አለ፡፡
በአምላክነቱ መለኮታዊ ባሕርይ ቢኖረውም እንደ ሰውነቱ ከእመቤታችን ከቅድስት ድንግል ማርያም ያለ ወንድ ዘር ተፀንሶ በድንግልና ተወልዷል። ቅዱስ ዮሐንስም በዘመኑ ለተነሱት ከሃዲያን የቅድስት ድንግል ማርያምን ዘለዓለማዊ ድንግልና አስረግጦ አስተምሮአል። አበው እንዳስተማሩን እግዚአብሔር ሰማይና ምድርን ከፈጠረበት ጥበቡ ይልቅ፣ ሰው ሆኖ ዓለምን ያዳነበት ጥበቡ ይበልጣል። ድንግል ማርያም ጌታን ከመፅነሷ በፊት በፀነሰች ጊዜ ከፀነሰችም በኋላ፤ እንዲሁም ከመውለዷ በፊት በወለደችም ጊዜ ከወለደችም በኋላ ድንግል ናት። ይህንንም እግዚአብሔር ስለገለጸለት ከአበይት ነቢያት መካከል አንዱ ቅዱስ ሕዝቅኤል በምዕራፍ 44÷1-4 “ወደ ምስራቅ ወደሚመለከተው በር አመጣኝ ይህ በርም ዝግ ነበር፣ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር ገብቶበታልና ለዘላለም ዝግ ሆኖ ይኖራል።” አለኝ ይላል፡፡
ምስራቅ ያላት ድንግል ማርያምን ነው ፀሐይ ከምስራቅ እንዲወጣ ጨለማውንም ዓለም ብርሃን እንዲያደርግ፤ ፀሐየ ጽድቅ ክርስቶስም ከአማናዊት ምስራቅ ከድንግል ማርያም ተልወዶ በኅጢያት ለጨለመው ዓለም የጽድቅ ብርሃን ሆኖ ተገልጧልና፡፡ ቅዱስ ጳውሎስም በገላትያ 4÷4 እንደጻፈው የዘመኑ ፍጻሜ በደረሰ ጊዜ እግዚአብሔር ያለ ወንድ ዘር ከቅድስት ድንግል ማርያም ከአምላክ እናት የተወለደውን አንድያ ልጁን ላከልን፣ እርሱም የእኛን ባህርይም ባህርይ አድርጎ ተወለደ። ልጆችም ስለሆንን እግዚአብሔር አባት ብለን የምንጠራበት የልጅነት መንፈስ ሰጠን፡፡ እመቤታችንም በሕቱም ድንግልና ይህን ጌታ ወለደችልን፡፡ ገዳማውያንም ይህችን እናት ዘወትር አማልጅን ይሏታል፡፡ ገዳማቸውን እደግፍ በዓታቸውን እናጽና፡፡
ድጋፍ ለማድረግ:- ሙትአንሳ ማር ቅዱሰ ሚካኤል አንድነት ገዳም
ኢትዮጲያ ንግድ ባንክ
1000442598391
ወይም
አቢሲኒያ ባንክ
141029444
የገዳሙ ስልክ ቁጥር:-0918077957 ወይም 0938644444
Source: GetuTemesgen









No comments yet.